ፊልጵስዩስ 1:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ብቻ ኑሩ፤ በዚህም መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል እምነት አብራችሁ መጋደላችሁንና በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁን እሰማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ፤ ይህ ከሆነ መጥቼ ባያችሁ ወይም በርቀት ሆኜ ስለ እናንተ ብሰማ፣ ለወንጌል እምነት እንደ አንድ ሰው ሆናችሁ በመጋደል በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ እንደምትቆሙ ዐውቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ የክርስቶስን ወንጌል የሚያስመሰግን ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁም ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ ዓላማ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ወንጌልን በኅብረት ለማዳረስ መጋደላችሁን እሰማለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ምናልባት የመጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳልኖርም ቢሆን በወንጌል ሃይማኖት እየተጋደላችሁ በአንድ መንፈስና በአንድ አካል ጸንታችሁ እንደምትኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራችሁ ለክርስቶስ ትምህርት እንደሚገባ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ። |
እርሱ ግን ሐሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው “እርስ በርስዋ የምትከፋፈል መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፤ እርስ በርስዋ የምትከፋፈል ከተማ ወይም ቤት ሁላ አትቆምም።
ከጥቂት ቀንም በኋላ ፊልክስ አይሁዳዊት ከነበረች ድሩሲላ ከሚሉአት ከሚስቱ ጋር መጥቶ ጳውሎስን አስመጣ፤ በኢየሱስ ክርስቶስም ስለ ማመን የሚናገረውን ሰማው።
ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፤ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደሆነ ማንም አልተናገረም።
በእግዚአብሔር ወንጌል እንደ ካህን እያገለገልሁ፥ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ እንድሆን ነው፥ ይህም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው የተወደደ መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው።
ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! ሁላችሁ ተስማምታችሁ በአንድ ልቡና እና በአንድ አቋም በአንድነት የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፤ ምክሬን ስሙ፤ በአንድ ልብ ሁኑ፤ በሰላም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
እንደ እነርሱ ከሆነ የማያምኑ ሰዎችን ልቦና፥ የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ አሳውሯል።
በዚህ አገልግሎት ስለ ተፈተናችሁ፥ በክርስቶስ ወንጌል በማመናችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ እነርሱንና ሁሉንም ስለምትረዱበት ልግስና፥ እግዚአብሔርን ያከብራሉ፤
እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል ሰምታችሁ፥ በክርስቶስም አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤
ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ ይበልጥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
በዚህም በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁና በእግዚአብሔር እውቀት እያደጋችሁ፥ ለጌታ እንደሚገባው ፍጹም ደስ የሚያሰኘውን ሕይወት እንድትኖሩ ነው።
አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ መልካም ዜና አመጣልን፤ እኛ እናንተን ለማየት እንደምንናፍቅ እናንተም እኛን ለማየት እንደምትናፍቁና ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱን ደግሞ ነገረን፤
እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መመላለስ እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ ተቀብላችኋል፤ በእርግጥም እየተመላለሳችሁ ነው፤ ከዚህም በበለጠ አብዝታችሁ እንድታደርጉት በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችኋለንም።
ይህን በምታደርግበት ጊዜ ግን እምነትንና በጎ ኅሊናን ይዘህ ይሁን፤ አንዳንዶች ሕሊናን ወደ ጎን በማድረግ፥ በእምነት ረገድ በማዕበል እንደተሰባበረች መርከብ ጠፍተዋል፤
ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለቅዱሳን ሁሉ ስለ ተሰጠው እምነት እንድትጋደሉ እንድመክራችሁና እንድጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።