Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 15:58 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

58 ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

58 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

58 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

58 አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

58 ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 15:58
42 Referencias Cruzadas  

መልካምን ሥራ ለመሥራት አንታክት፥ ካልዛልን ወቅቱ በደረሰ ጊዜ እናጭዳለንና።


እናንተ ግን ለሥራችሁ ሽልማት ይሆንላችኋልና በርቱ፥ እጃችሁም አይላላ።”


እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።


እናንተም የሕይወትን ቃል በጽኑ በመያዛችሁ ምክንያት በከንቱ እንዳልሮጥሁ በከንቱም እንዳልደከምሁ በክርስቶስ ቀን የምመካበት ነገር ይሆንልኛል።


የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ክፍያ ይቀበላል።


ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት የምትጸኑ ከሆነ ነው፤ ይህም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፤ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።


በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት የእምነታችሁን ሥራ፥ የፍቅራችሁን ድካም፥ በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን የተስፋችሁንም መጽናት እናስታውሳለን።


አፉ ከቅቤ ይልቅ ለዘበ፥ በልቡ ውስጥ ግን ጦርነት ነበረ፥ ቃሎቹም ከዘይት ይልቅ ለሰለሱ፥ ነገር ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ናቸው።


በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ትፈጽሙ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


ጢሞቴዎስ ወደ እናንተ ከመጣ፥ እርሱም እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና፥ አብሮአችሁ ያለ ሥጋት እንዲቀመጥ አድርጉ።


ጌታ እንድትበዙ ያድርጋችሁ፤ እኛም ለእናንተ ፍቅርን እንዳበዛንላችሁ እንዲሁም የእርስ በርሳችሁንና ለሁሉ ሰው ያላችሁን ፍቅር ያብዛ።


አብዝታችሁ ምስጋናን በማቅረብ እንደ ተማራችሁት ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፤ በእምነትም ጽኑ።


ለዘለዓለም አይናወጥም፥ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል።


እንግዲህ ወዳጆች ሆይ! ይህ ተስፋ ቃል ስላለን፥ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፥ እግዚአብሔርን በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርግ።


እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መመላለስ እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ ተቀብላችኋል፤ በእርግጥም እየተመላለሳችሁ ነው፤ ከዚህም በበለጠ አብዝታችሁ እንድታደርጉት በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችኋለንም።


መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ስለዚህ ወዳጆች ሆይ! ይህን ሁሉ እየተጠባበቃችሁ፥ ጌታ ያለ ነውር ወይም ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም እንዲያገኛችሁ በትጋት ኑሩ፤


በአካል ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፤ መልካሙንም ሥነ ሥርዓታችሁንና በክርስቶስም ላይ ያላችሁን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል።


የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤


በዚህ መከራ ማንም እንዳይናወጥ፥ ለዚህ እንደ ተሾምን ራሳችሁ ታውቃላችሁና።


ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ እጸልያለሁ፤


ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ አድጎአልና፥ የእናንተም የእያንዳንዳችሁ ሁሉ ፍቅር ለእርስ በርሳችሁ በዝቶአልና፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግዴታ አለብን፤


ከወርቅና ከክቡር ዕንቁ ይልቅ ይወደዳል፥ ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል።


ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኝ የጽድቅ ፍሬ የተሞላችሁ እንድትሆኑ ነው።


ከጥሪታችሁ የሚበዛውን ፍሬ እንጂ ስጦታን ፈላጊ አይደለሁም።


ምናልባት ስለ እናንተ በከንቱ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።


ከእርሷ ጋር ለመሄድ እንደ ቈረጠች ባየች ጊዜ ናዖሚ ከመናገር ዝም አለች።


ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት ለመታገስ ባልተቻለኝ ጊዜ፦ “ፈታኙ ምናልባት ፈትኖአቸዋል፤ ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል፤” ብዬ በመፍራት እምነታችሁን ለማወቅ ጢሞቴዎስን ላክሁ።


ምክንያቱም እናንተ ልትሰጡኝ ያልቻላችሁትን አገልግሎት ለመፈጸም ሕይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ ለክርስተቶስ ሥራ ሲል ለሞት ተቃርቦ ነበርና።


እንደ አባቶቻቸው እንዳይሆኑ ዐመፀኛና የሚያስመርር ትውልድ፥ ልቡን ያላቀና ትውልድ፥ መንፈሱም በእግዚአብሔር ዘንድ ያልታመነ።


እንዲህም አልሁ፦ በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ።


ልባቸውም ከእርሱ ጋር አልቀናም፥ ለቃል ኪዳኑም አልታመኑም።


ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ጽድቅን ክብርንም ያገኛል።


ይህንኑ ቃል አራት ጊዜ ላኩብኝ፤ እኔም ይህንኑ ቃል መለስኩላቸው።


እርሱም እጁ የሰለለችውን ሰው “ተነሥ! በመካከል ቁም” አለው።


ይህናውንም ‘አንተንም በአምስት ከተማዎች ላይ ሾሜሃለው፤’ አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios