Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 1:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በወንጌል አላፍርምና፤ በመጀመሪያ ለአይሁድ እንዲሁም ለግሪካውያን፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ ይህም በመጀመሪያ ለአይሁድ፣ ቀጥሎም ለአሕዛብ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኔ በወንጌል ቃል አላፍርም፤ የወንጌል ቃል በመጀመሪያ አይሁድን፥ ቀጥሎም አሕዛብን፥ እንዲሁም የሚያምኑትን ሰዎች ሁሉ ማዳን የሚችል የእግዚአብሔር ኀይል ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ተ​ማር አላ​ፍ​ር​ምና፤ አስ​ቀ​ድሞ አይ​ሁ​ዳ​ዊን፥ ደግ​ሞም አረ​ማ​ዊን፥ የሚ​ያ​ም​ኑ​በ​ትን ሁሉ የሚ​ያ​ድ​ና​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይሉ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 1:16
38 Referencias Cruzadas  

በዚህ ዘማዊና ኀጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅም በአባቱ ግርማ፥ ከቅዱሳን መላእክት ጋር ሲመጣ ያፍርበታል።”


እንግዲህ ስለ ጌታችን ምስክርነት በመስጠት ወይም ስለ እርሱ በታሰርሁ በእኔ አትፈር ይልቁንም እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል።


ክርስቲያን በመሆኑ መከራ ቢደርስበት ግን ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።


በዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ እቀበላለሁ፤ ነገር ግን ያመንኩትን አውቃለሁና አላፍርበትም፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ለመጠበቅ እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ።


በእኔና በቃሎቼ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ በክብሩና በአባቱ ክብር እንዲሁም በቅዱሳን መላእክቱ ክብር በሚመጣበት ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።


እንደ እነርሱ ከሆነ የማያምኑ ሰዎችን ልቦና፥ የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ አሳውሯል።


ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤


በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር፥ እርሱም እንደ ተሰቀለ፥ ሌላ ነገር ላለማወቅ ወስኜ ነበርና።


ስለዚህ እምነት የሚመጣው ከመስማት ነው፤ መስማትም በክርስቶስ ቃል በኩል ነው።


የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፤ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፤ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ዘልቆ ይወጋል፤ የልብንም አሳብና ትኩረት ይመረምራል፤


የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፥ ያመናችሁት በከንቱ ካልሆነ በስተቀር፥ የምትድኑበትን ወንጌል ነው።


በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል ጌታ።


ሌላ ወንጌል ያለ አይምሰላችሁ፤ የሚያናውጡአችሁና የክርስቶስንም ወንጌል ለማጣመም የሚፈልጉ አንዳንዶች አሉ።


ክፉ በሚያደርግ ሰው ሁሉ ላይ፥ አስቀድሞ በአይሁዳዊ ከዚያም በግሪካዊ መከራና ጭንቀት ይሆንበታል፤


ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ ላከው።”


በነገሥታት ፊት ምስክርህን እናገራለሁ፥ አላፍርምም፥


ስለዚህም የመልእክትን ቃል፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በአማኞች ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።


የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የጌታስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?


ይህም ትምህርት ለእኔ በአደራ ከተሰጠኝ ከብሩክ እግዚአብሔር ክቡር ወንጌል ጋር የሚስማማ ነው።


በዚህ አገልግሎት ስለ ተፈተናችሁ፥ በክርስቶስ ወንጌል በማመናችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ እነርሱንና ሁሉንም ስለምትረዱበት ልግስና፥ እግዚአብሔርን ያከብራሉ፤


የክርስቶስን ወንጌል ለመስበክ ወደ ጢሮአዳ በመጣሁ ጊዜ፥ በጌታ በሩ ተከፍቶልኝ ነበር፤


እንግዲህ ዋጋዬ ምንድነው? በወንጌል ካለኝ መብት በሙሉ ሳልጠቀምበት ወንጌልን እየሰበክሁ ወንጌልን ያለ ክፍያ ባስተምር ነው።


ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን የመካፈል መብት ያላቸው ከሆነ፥ እኛማ ይልቁን አይኖረንም? በዚህ መብት ግን አልተጠቀምንም፥ ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል በምንም እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ።


ወደ እናንተም ስመጣ በክርስቶስ በረከት ሙላት እንደምመጣ አውቃለሁ።


በምልክትና በድንቅ ሥራ ኃይል፥ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል፥ ከኢየሩሳሌም ጀምሬ እስከ እልዋሪቆን ድረስ እየዞርሁ የክርስቶስን ወንጌል ፈጽሜ ሰብኬአለሁ።


ጌታ ለሄኔሲፎሩ ቤተሰብ ምሕረትን ይስጥ፤ ብዙ ጊዜ አሳርፎኛልና፤ በሰንሰለቴም አላፈረበትም፤


ሳይገረዝም በእምነቱ ባገኘው የጽድቅ ማኅተም፥ መገረዝን እንደ ምልክት ተቀበለ፤ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ፥ ለእነርሱም ጽድቅ ሆኖ እንዲቆጠርላቸው አባት ነውና፤


ጌታ የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል፥ በጠላቶችህም መካከል ግዛ።


አይሁድም እንዲህ ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፤ “እኛ እንዳናገኘው ይህ ሰው ወዴት ሊሄድ ነው? በግሪክ ሰዎች መካከል ተበትነው ወደሚኖሩት ሄዶ የግሪክን ሰዎች ሊያስተምር ነውን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios