ዘሌዋውያን 24:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መልካሙንም ዱቄት ውሰድ፤ በእርሱም ዐሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር፤ በአንድ ኅብስት ውስጥ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ይደረግበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የላመ ዱቄት ወስደህ ዐሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር፤ እያንዳንዱ ኅብስትም በሁለት ዐሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት ይጋገር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዐሥራ ሁለት ኪሎ የላመ ዱቄት ወስደህ ዐሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የስንዴ ዱቄት ወስደህ ዐሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር፤ በእያንዳንዱ ኅብስት ውስጥ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልካሙንም ዱቄት ወስደህ አሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር፤ በአንድ ኅብስት ውስጥ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ ይሁን። |
ደግሞም የተቀደሰ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም፥ ለእህል ቁርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በመለክያ ሁሉ ያገልግሉ ነበር።
በየጥዋቱና በየማታውም ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መዓዛው ያማረ ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የተቀደሰውንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የጌታን ትእዛዝ እንጠብቃለን፥ እናንተ ግን ትታችሁታል።
ለአምላካችን ቤት አገልግሎት የሚውል አንድ ሦስተኛ ሰቅል በየዓመቱ ለመስጠት በራሳችን ላይ ትእዛዝ እናስቀምጣለን። ስለ ገጸ ኅብስትም፥ ዘወትርም በሰንበትና በመባቻ ስለ ማቅረብ ስለ እህሉ ቁርባንና ስለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ በዓላትም፥ ስለ ተቀደሱትም ነገሮች፥ ለእስራኤልም ስለሚያስተሰርየው ስለ ኃጢአት መሥዋዕት፥ ስለ አምላካችንም ቤት ሥራ ሁሉ በየዓመቱ የሰቅል ሢሶ እናመጣ ዘንድ ትእዛዝ በራሳችን ላይ አደረግን።
እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቁርባን ዕጣ ተጣጣልን፥
በተቀደሰው ኅብስቱ ገበታ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ሙዳዮችንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለመጠጥ ቁርባንም መንቀሎቹን ያስቀምጡበት፤ ሁልጊዜም የሚቀርበው እንጀራ በእርሱ ላይ ይሁን።
ወደዚህም ወደ ተስፋ ቃል ዐሥራ ሁለቱ ወገኖቻችን ሌሊትና ቀን በትጋት እያመለኩ ይደርሱ ዘንድ አለኝታ አላቸው፤ ስለዚህም አለኝታ፥ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! ከአይሁድ እከሰሳለሁ።
ስለዚህ ካህኑ የተቀደሰውን እንጀራ ለዳዊት ሰጠው፤ ከጌታ ፊት ተነሥቶ በትኩስ እንጀራ ከተተካው ከኅብስት በስተቀር በዚያ ሌላ እንጀራ አልነበረምና።