Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 18:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ጌታ ከዚያ በፊት “እስራኤል” ብሎ ከሰየመው ከያዕቆብ በተወለዱት በዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከዚያም ኤልያስ፣ “ስምህ እስራኤል ይባላል” ተብሎ የእግዚአብሔር ቃል በመጣለት በያዕቆብ ልጆች ነገድ ቍጥር ልክ ዐሥራ ሁለት ድንጋይ ወስዶ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እግዚአብሔር ከዚያ በፊት “እስራኤል” ብሎ ከሰየመው ከያዕቆብ በተወለዱት በዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ወሰደ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ኤል​ያ​ስም፦ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይሆ​ናል የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ደረ​ሰ​ለት እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ቍጥር ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ኤልያስም “ስምህ እስራኤል ይሆናል፤” የሚል የእግዚአብሔር ቃል እንደ ደረሰለት እንደ ያዕቆብ ልጆች ነገድ ቁጥር ዐሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 18:31
17 Referencias Cruzadas  

ሰውየውም፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና እስራኤል ይባላል” አለው።


ያዕቆብም፦ “ልለምንህ፥ ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው። እርሱም፦ “ስሜን ለምን ትጠይቃለህ?” አለው። በዚያም ስፍራ ባረከው።


እዚያም መሠውያውን አቆመ፥ ያንም ኤል ኤሎሄ እስራኤል ብሎ ጠራው።


እግዚአብሔርም፦ “ስምህ ያዕቆብ ነው፥ ከእንግዲህም ወዲህ፥ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ፥ ስምህ ያዕቆብ ተብሎ አይጠራ፥” አለው። ስሙንም እስራኤል ብሎ ጠራው።


ይህንኑ አሮጌ ልማዳቸውን እስከ አሁን ድረስ በመፈጸም ላይ ናቸው፤ እነርሱ እግዚአብሔርን አያመልኩም፤ ወይም ስሙ እስራኤል ተብሎ ለተጠራው ለያዕቆብ ልጆች እግዚአብሔር በሰጣቸው ደንቦች፥ ሥርዓቶች፥ ሕጎችና ትእዛዞች ጸንተው አልኖሩም።


ለዚህ የእግዚአብሔር ቤት ምረቃ አንድ መቶ ወይፈኖች፥ ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶ የበግ ጠቦቶችን፥ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት እንደ እስራኤል ነገዶች ቍጥር ለእስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ።


ሙሴም የጌታን ቃሎች ሁሉ ጻፈ፤ በማለዳ ተነሥቶ ከተራራው በታች መሠዊያንና ዐሥራ ሁለት ሐውልቶች ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ።


እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ ከይሁዳም ውኆች የወጣችሁ፥ በጌታ ስም የምትምሉ፥ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ፥


በዚያን ዘመን፥ ይላል ጌታ፥ ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ርስት አድርጋችሁ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ምድሪቱን የምትከፍሉበት ድንበር ይህ ነው። ለዮሴፍ ሁለት ድርሻ ይሆናል።


በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤


ከዮርዳኖስም ውስጥ የወሰዱአቸውን እነዚያን ዐሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ኢያሱ በጌልገላ አኖራቸው።


ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፤ ዐሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት፤ በደጆቹም ዐሥራ ሁለት መላእክት ቆመው ነበር፤ የዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos