ሰቈቃወ 5:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ልባችን ታምሞአል፥ ስለዚህም ነገር ዓይናችን ፈዝዞአል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ የተነሣ ልባችን ደከመ፤ ከእነዚህ የተነሣም ዐይናችን ፈዘዘ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ምክንያት ልባችን ታመመ፤ በእነዚህም ነገሮች ምክንያት ዐይኖቻችን ደከሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ልባችን ታምሞአል፤ ስለዚህም ነገር ዐይናችን ፈዝዞአል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ልባችን ታምሞአል፥ ስለዚህም ነገር ዓይናችን ፈዝዞአል፥ |
እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፥ እንደ ርግብም አጉረመረምሁ፤ ዐይኖቼ ወደ ላይ በማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፥ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ።
ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኃያላኖቻቸውም ሲደበደቡ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዚህና በዚያ ድንጋጤ አለ፥ ይላል ጌታ።
ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማይቱ ጐዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዓይኔ በእንባ ደከመች፥ አንጀቴም ታወከ፥ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ጉበቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ።
ልብ እንዲቀልጥ፥ ብዙዎች እንዲሰናከሉ ነው፤ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ የሚገድል ሰይፍ አድርጌአለሁ፥ ወዮ! እንዲያብረቀርቅ ተወልውሎአል፥ እንዲገድልም ተጠቅልሎአል።
እነርሱም ለምን ታለቅሳለህ? ሲሉህ እንዲህ በላቸው፦ ወሬ ስለሚመጣ ነው፥ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፥ እጆች ሁሉ ይዝላሉ፥ ነፍስ ሁሉ ትደክማለች፥ ጉልበት ሁሉ እንደ ውኃ ይፈስሳል፥ እነሆ ይመጣል ይፈጸማልም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ መካከል በተረፉት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እልክባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታስደነብራቸዋለች፤ እነርሱም ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።
በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ ቦታ አይኖርም። በዚያም ጌታ የሚርድ ልብ፥ ፈዛዛ ዐይኖች፥ ደካማም ነፍስ ይሰጥሃል።