ሕዝቅኤል 21:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እነርሱም ለምን ታለቅሳለህ? ሲሉህ እንዲህ በላቸው፦ ወሬ ስለሚመጣ ነው፥ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፥ እጆች ሁሉ ይዝላሉ፥ ነፍስ ሁሉ ትደክማለች፥ ጉልበት ሁሉ እንደ ውኃ ይፈስሳል፥ እነሆ ይመጣል ይፈጸማልም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እነርሱም፣ ‘ለምን ታቃስታለህ?’ ቢሉህ፣ ‘ስለሚመጣው ክፉ ወሬ ነው፤ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፤ እጅም ሁሉ ይዝላል፤ ነፍስ ሁሉ ይደክማል፤ ጕልበትም ሁሉ ውሃ ይሆናል’ በላቸው። እነሆ፤ ይመጣል፤ ይፈጸማልም ይላል ጌታ እግዚአብሔር።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 “ለምን ትቃትታለህ” ብለው ቢጠይቁህ “ስለሚመጣው ወሬ ነው” ትላቸዋለህ፤ “በዚያም ወሬ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፤ እጅ ሁሉ ይዝላል፤ ወኔ ሁሉ ይከዳል፤ ጒልበት ሁሉ እንደ ውሃ ይፈስሳል፤ እነሆ እየመጣ ነው፤ በእርግጥ ይፈጸማል” ይላል ልዑል እግዚአብሔር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 እነርሱም፦ ስለ ምን ታለቅሳለህ? ቢሉህ አንተ እንዲህ በላቸው፦ ስለሚመጣው ወሬ ነው፤ ልብም ሁሉ ይቀልጣል፤ እጆችም ሁሉ ይዝላሉ፤ ሥጋና መንፈስ ሁሉ ይደክማል፤ ከጕልበትም እዥ ይፈስሳል፤ እነሆ ይመጣል፤ ይፈጸማልም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እነርሱም፦ ስለ ምን ታለቅሳለህ? ቢሉህ፥ አንተ እንዲህ በላቸው፦ ወሬ ስለሚመጣ ነው፥ ልብም ሁሉ ይቀልጣል፥ እጆችም ሁሉ ይዝላሉ፥ ነፍስም ሁሉ ትደክማለች፥ ጉልበትም እንደ ውኃ ይፈስሳል፥ እነሆ፥ ይመጣል ይፈጸምማል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítulo |