Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 21:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ልብ እንዲቀልጥ፥ ብዙዎች እንዲሰናከሉ ነው፤ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ የሚገድል ሰይፍ አድርጌአለሁ፥ ወዮ! እንዲያብረቀርቅ ተወልውሎአል፥ እንዲገድልም ተጠቅልሎአል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ልብ ሁሉ ይቀልጥ ዘንድ፣ የሚወድቁትም እንዲበዙ፣ በበሮቻቸው ሁሉ፣ የግድያውን ሰይፍ አኑሬአለሁ። ወዮ! እንዲያብረቀርቅ ተወልውሏል፤ ለመግደልም ተመዝዟል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሕዝቤ በፍርሃት በመሞላት ተሰናክለው ይወድቃሉ፤ እንደ መብረቅ በሚያብለጨልጭ፥ ለመግደያ የተዘጋጀውን ሰይፍ፥ በየበራፋቸው አድርጌአለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ልባ​ቸው እን​ዲ​ቀ​ልጥ፥ መሰ​ና​ክ​ላ​ቸ​ውም እን​ዲ​በዛ የሚ​ገ​ድ​ለ​ውን ሰይፍ በበ​ሮ​ቻ​ቸው ሁሉ ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ወዮ! ያብ​ረ​ቀ​ርቅ ዘንድ ተሰ​ን​ግ​ሏል፤ ይገ​ድ​ልም ዘንድ ተስ​ሏል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ልባቸው እንዲቀልጥ መሰናክላቸውም እንዲበዛ የሚገድለውን ሰይፍ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ አድርጌአለሁ፥ ወዮ! ያብረቀርቅ ዘንድ ተሰንግሎአል ይገድልም ዘንድ ተስሎአል።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 21:15
15 Referencias Cruzadas  

አባትህ ታላቅ ጦረኛ፥ አብረውት ያሉትም ጀግኖች መሆናቸውን እስራኤል ሁሉ ስለሚያውቅ፥ ልቡ እንደ አንበሳ ልብ የሚደፍረው እንኳ በፍርሀት ይርዳል።


እንደ ነጣቂና እንደሚያገሣ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ።


እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመስን፥ ዐይን እንደሌላቸው ተርመሰመስን፤ በቀትር ጊዜ በድግዝግዝታ እንዳለ ሰው ተሰናከልን፥ እንደ ሙታን በጨለማ ስፍራ ነን።


ሳትጨልም እግራችሁም በጨለሙት ተራሮች ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨልማ ሳይለውጠው፥ ለአምላካችሁ ለጌታ ክብርን ስጡ።


ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፥ አትጠፋምም።’ ”


ሕዝቤ ግን ረስተውኛል ለከንቱ ነገርም ዐጥነዋል፤ ከመንገዳቸውም አሰናክለዋቸዋል ከቀድሞውም ጐዳና ርቀው ወዳልተሠራው ወደ ጠማማው መንገድ ሄደዋል።


ፊቴን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ከእሳት ቢያመልጡም፥ እሳት ግን ይበላቸዋል፥ ፊቴን በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ለደቡብም ዱር፦ የጌታን ቃል ስማ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በአንተ ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፤ በውስጥህም ያለውን የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍ ሁሉ ይበላል፤ የሚቃጠል ነበልባል አይጠፋም፤ ከደቡብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃጠልበታል።


እንዲገድል ተስሎአል እንዲያብረቀርቅም ተወልውሏል፥ እኛስ ደስ ይለናልን? የልጄን በትር እንደ ማንኛውም ዛፍ ንቆታል።


ተዘጋጅተህ ፊትህ ወደ ወደደው ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ሂድ።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ የሚመጣበትን ሁለት መንገዶችን አድርግ፥ ሁለቱም ከአንዲት ምድር ይውጡ፥ ምልክትም አድርግ፥ በከተማይቱ መንገድ ራስ ላይ አድርገው።


የቅጥሩን ማፍረሻ ያደርግ ዘንድ፥ አፍንም በጩኸት ይከፍት ዘንድ፥ በውካታም ድምፅን ከፍ ያደርግ ዘንድ፥ የቅጥሩን ማፍረሻ በበሮች ላይ ያደርግ ዘንድ፥ አፈርን ይደለድል ዘንድ፥ ምሽግም ይሠራ ዘንድ የኢየሩሳሌም ዕጣ በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፦ ጌታ እግዚአብሔር ስለ አሞን ልጆችና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል ብለህ ትንቢት ተናገር፤ ቀናቸው በደረሰ፥ የኃጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ በደረሰ፥ በተገደሉት ኃጢአተኞች


እነርሱም ለምን ታለቅሳለህ? ሲሉህ እንዲህ በላቸው፦ ወሬ ስለሚመጣ ነው፥ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፥ እጆች ሁሉ ይዝላሉ፥ ነፍስ ሁሉ ትደክማለች፥ ጉልበት ሁሉ እንደ ውኃ ይፈስሳል፥ እነሆ ይመጣል ይፈጸማልም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ይህንንም ነገር ሰምተን ልባችን ቀለጠ፤ ጌታ አምላካችሁም በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከእግዲህ ወዲያ ሰው ሁሉ ሐሞተ ቢስ ሆኖአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos