ኢዮብ 7:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀኖቼ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ይቸኩላሉ፥ ያለ ተስፋም ያልቃሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዘመኔ ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ ይፈጥናል፤ ያለ ተስፋም ያልቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዕድሜዬ ቀኖች ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ ይፈጥናሉ፤ ያለ አንዳች ተስፋም ወደ ፍጻሜ ይደርሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወቴ እንደ ሸማኔ መወርወርያ፥ ቀላል ሆነች በከንቱ ተስፋም ጠፋሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘመኔ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ይቸኵላል፥ ያለ ተስፋም ያልቃል። |
በባዶ እግርሽ ከመሄድ፥ ጉሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፤ አንቺ ግን፦ ‘ተስፋ የለኝም፥ አይሆንም! እንግዶችን ወድጄአለሁና፥ እከተላቸዋለሁም’ አልሽ።
በዚያ ዘመን በዚህም ዓለም ያለ ክርስቶስ ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ፥ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፥ ተስፋን አጥታችሁና ከእግዚአብሔር ተለይታችሁ እንደ ነበር አስታውሱ።