ኢዮብ 34:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥራቸውን ያውቃል፥ በሌሊት ይገለባብጣቸዋል፤ እነርሱም ይደቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ሥራቸውን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ በሌሊት ይገለብጣቸዋል፤ እነርሱም ይደቅቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ሥራቸውን ዐውቆ፥ በአንድ ሌሊት ከሥልጣናቸው አስወግዶ ያጠፋቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥራቸውን ያውቃል፥ በእነርሱም ላይ ሌሊትን ያመጣል፥ መከራንም ያጸናባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥራቸውን ያውቃል፥ እንዲደቅቁም በሌሊት ይገለባብጣቸዋል። |
ሙታንን፥ እንዲሁም ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት በተጻፈው መሠረት፥ እንደ ሥራቸው መጠን ፍርድን ተቀበሉ።