Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 34:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እነርሱ በእኩለ ሌሊት በድንገት ይሞታሉ፥ ሕዝቡ ተንቀጥቅጦ ያልፋል፥ ኃያላንም ያለ ምንም ድካም ይወገዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እነርሱም እኩለ ሌሊት ላይ በድንገት ይሞታሉ፤ ሕዝብ ተንቀጥቅጦ ሕይወቱ ያልፋል፤ ኀያላኑም የሰው እጅ ሳይነካቸው ይወገዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሰዎች በእኩለ ሌሊት በቅጽበት ሊሞቱ ይችላሉ። ተንቀጥቅጠውም ያልፋሉ። ኀያላንም የማንም ሰው እጅ ሳይነካቸው ይወገዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የሚ​ጮ​ኸ​ው​ንና ሰውን የማ​ይ​ሰ​ማ​ውን ከንቱ ነገር ያገ​ኘ​ዋል፥ በድ​ሆች ላይ ክፉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እነርሱ በመንፈቀ ሌሊት በድንገት ይሞታሉ፥ ሕዝቡ ተንቀጥቅጦ ያልፋል፥ ኃያላንም ያለ እጅ ይነጠቃሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 34:20
25 Referencias Cruzadas  

ካህናትን እንደ ምርኮኛ ይወስዳቸዋል፥ ኃያላንንም ይገለብጣቸዋል።


ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ታገኘዋለች፥ በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ትነጥቀዋለች።


ሥራቸውን ያውቃል፥ በሌሊት ይገለባብጣቸዋል፤ እነርሱም ይደቃሉ።


ሰዎች ድንገት የሚሞቱበትን ሌሊትን አትመኛት።


እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥ በድንጋጤ ጠፉ።


ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።


የጌታም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።


በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፤ ወደ አራራትም አገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፈንታ ነገሠ።


መስፍኖችንም እንዳልነበሩ፥ የምድርንም ፈራጆች እንደ ከንቱ ነገር የሚያደርጋቸው እርሱ ነው።


እርሱም መልሶ፦ “ለዘሩባቤል የተባለው የጌታ ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


እኩል ሌሊት በሆነ ጊዜ ‘እነሆ ሙሽራው፤ ልትቀበሉት ውጡ’ የሚል ጩኸት ተሰማ።


እግዚአብሔር ግን ‘አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል?’ አለው።


ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያንጊዜ የጌታ መልአክ መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።


የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ የሚመጣ መሆኑን እናንተው ራሳችሁ በጥንቃቄ አውቃችኋልና።


ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ፍርዳቸውም ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!


ሕያው ጌታ አለ፥ ጌታ ራሱ ይቀሥፈዋል፤ ወይም የመሞቻው ቀን ይመጣል፤ ወይም በጦርነት ይሞታል፤ ይጠፋልም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos