Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -


ማሕልየ መሓልይ 3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሌሊት በመኝታዬ ላይ ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፥ ፈለግሁት አላገኘሁትም።

2 እነሣለሁ በከተማይቱም እዞራለሁ፥ ነፍሴ የወደደችውን በጎዳናና በአደባባይ እፈልጋለሁ፥ ፈለግሁት አላገኘሁትም።

3 ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥ ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? አልኋቸውም።

4 ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትም ወደ እናቴም ቤት ወደ ወለደችኝም እልፍኝ እስካገባው ድረስ አልተውሁትም።

5 እናንተ የኢየሩሳሌም ቈንጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ፥ ፍቅርን እንዳታስነሡትና እንዳታነሣሡት በሚዳቋ በምድረ በዳም ዋላ አስምላችኋለሁ።

6 መዓዛም እንደ ከርቤና እንደ ዕጣን የሆነችው፥ ከልዩ ከነጋዴ ቅመም ሁሉ የሆነችው፥ ይህች ከምድረበዳ እንደ ጢስ ምስሶ የወጣችው ማን ናት?

7 እነሆ፥ የሰሎሞን አልጋ ናት፥ ከእስራኤል ኃያላን መካከል ስድሳ ኃያላን በዙሪያው ናቸው።

8 ሁሉም ሰይፍ የያዙና ጦርነት የለመዱ ናቸው፥ በሌሊት ከሚከሰት አደጋ የተነሣ ሰው ሁሉ ሰይፉ በወገቡ አለ።

9 ንጉሡ ሰሎሞን መቀመጫ ከሊባኖስ እንጨት ለራሱ አሠራ።

10 ምሰሶቹን የብር፥ መደገፊያውንም የወርቅ፥ መቀመጫውንም ሐምራዊ ግምጃ አደረገ፥ ውስጡ በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ፍቅር የተለበጠ ነው።

11 እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት፥ ውጡ፥ እናቱ በሰርጉ ቀንና በልቡ ደስታ ቀን ያደረገችለትን አክሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎሞንን እዩ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos