ኢዮብ 33:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ አንተ በዚህ አቋምህ ትክክል አይደለህም፥ ‘እግዚአብሔር ከሰው ይበልጣል’ ብዬ እመልስልሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነገር ግን እግዚአብሔር ከሰው ስለሚበልጥ፣ ትክክል እንዳልሆንህ እነግርሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኢዮብ ሆይ! ይህ ንግግርህ ስሕተት መሆኑን ልገልጥልህ እወዳለሁ፤ እግዚአብሔር ከሰው ሁሉ ይበልጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ቃሌንም አይሰማኝም እንዴት ትላለህ? ከሟች ሰው በላይ ያለ እርሱ ዘለዓለማዊ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ አንተ በዚህ ጻድቅ አይደለህም፥ እግዚአብሔር ከሰው ይበልጣል ብዬ እመልስልሃለሁ። |
“የእስራኤል ቤት ሆይ! ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ላይ መሥራት አልችልምን? ይላል ጌታ፤ እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ የእስራኤል ቤት ሆይ! እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ አላችሁ።
እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ ቀና አይደለም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ ስሙ፥ በውኑ መንገዴ ቀና አይደለምን? ቀና ያልሆነውስ የእናንተ መንገድ አይደለምን?