ኢዮብ 20:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አጥንቶቹ በወጣት ኃይል ተሞልተው ነበር፥ ነገር ግን አሁን ያ የወጣትነት ኃይሉ ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐጥንቱን የሞላው የወጣትነት ብርታት፣ ከርሱ ጋራ በዐፈር ውስጥ ይተኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይል የተሞላው የወጣትነት ሰውነቱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዐፈር ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጭንቀት በአጥንቶቹ ሞልቶአል፤ ነገር ግን ሕማሙ ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጥንቶቹ ብላቴንነቱን ሞልተዋል፥ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል። |
በርኩሰትሽ ሴሰኝነት አለ፥ መዓቴን በአንቺ ላይ እስክጨርስ ድረስ ከእንግዲህ ወዲያ ከርኩሰትሽ ንፁህ አትሆኚም ምክንያቱም አነጻሁሽ ነገር ግን ንፁህ አልሆንሺምና።
ከወደቁ ኃያላን ካልተገረዙ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው፥ ሰይፋቸውንም ከራስጌያቸው በታች አድርግው ወደ ሲኦል ከወረዱ ጋር አልተኙም፥ በሕያዋንም ምድር ያሸብሩ ስለ ነበር ኃጢአታቸውም በአጥንታቸው ላይ ነበር