ኢሳይያስ 59:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፥ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው፥ ጉስቁልናና ውድመት በሚሄዱበት አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግሮቻቸው ወደ ኀጢአት ይሮጣሉ፤ ንጹሕ ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ የሚያስቡት ክፉ ሐሳብ ነው፤ በመንገዶቻቸው ጥፋት እና መፍረስ ይገኛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ወደ ክፉ ሥራ ይሮጣሉ፤ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ ይቸኲላሉ፤ ሐሳባቸው የበደል ሐሳብ ነው፤ በሚያልፉበት ቦታ ሁሉ ማጥፋትና ማፈራረስ ልማዳቸው ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግሮቻቸውም ለተንኮል ይሮጣሉ፤ ደምን ለማፍሰስም ይፈጥናሉ፤ ሰውን ለመግደል ይመክራሉ፤ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፥ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፥ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው፥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ። |
ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ከእርሷ የሚሸሹ ወደ ዞዐር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኮበለሉ፤ በሉሒት አቀበት ላይ እያለቀሱ ወጡ፤ በሖሮናይምም መንገድ የዋይታ ጩኽት አሰሙ።
ሰነፍ ግን የስንፍናን ነገር ይናገራል፤ ልቡም በጌታም ላይ ስህተትን ለመናገር፥ የተራበችውንም ሰውነት ረሃቡን እንዳያስታግስ፥ የተጠማም ሰው ጥሙን እንዳይቆርጥ በደልን ለመሥራት ክፋትን ያቅዳል።
እኔ ደግሞ የተሳለቀባቸውን እመርጣለሁ፥ የፈሩትንም ነገር አመጣባቸዋለሁ። ምክንያቱም በፊቴ ክፉ ነገርን አድርገዋል፥ ያልወደድሁትንም መርጠው በጠራኋቸው ጊዜ አልመለሱልኝም፤ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝም።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።
ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፥ ወታደሮችን ልኮ ከሰብአ ሰገል በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን በቤተ ልሔምና በአካባቢዋ የነበሩትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።