Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 18:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ድሀውንና ችግረኛውን ቢያስጨንቅ፥ ቢቀማ፥ መያዣውን ባይመልስ፥ ዐይኖቹን ወደ ጣዖታት ቢያነሣ፥ ርኩሰትን ቢያደርግ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ድኻውንና ችግረኛውን ቢጨቍን፣ በጕልበት ቢቀማ፣ በመያዣነት የወሰደውን ባይመልስ፣ ወደ ጣዖታት ቢመለከት፣ አስጸያፊ ተግባራትን ቢፈጽም፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ድኾችንና ችግረኞችን ቢያስጨንቅ፥ ቢቀማ፥ ገንዘብ ሲያበድር በመያዣ ስም የወሰደውን ቢያስቀር፥ በአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎች ጣዖትን ቢያመልክ አጸያፊ ነገሮችን ቢያደርግ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ድሀ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ውን ቢያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ቢቀ​ማም፥ መያ​ዣ​ው​ንም ባይ​መ​ልስ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ጣዖ​ታት ቢያ​ነሣ፥ ርኩ​ስ​ንም ነገር ቢያ​ደ​ርግ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ድሀውንና ችግረኛውንም ቢያስጨንቅ ቢቀማም መያዣውንም ባይመልስ ዓይኖቹንም ወደ ጣዖታት ቢያነሣ ርኩስን ነገር ቢያደርግ፥

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 18:12
19 Referencias Cruzadas  

“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፤


እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከርኲሰት ተራራ በስተ ደቡብ ዐስታሮት ተብላ ለምትጠራው ለሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞዓብ አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞን አምላክ ንጉሥ ሰሎሞን አሠርቶአቸው የነበሩት አጸያፊዎች ምስሎች ሁሉ የረከሱ መሆናቸውን አስገነዘበ።


ጌታ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤


ዓይንህና ልብህ ግን ለተጭበረበረ ትርፍ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ነው።”


ጌታ እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም አትበድሉ፥ አታምፁባቸውም፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።


እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም በደል ይህ ነበር፤ በእርሷና በሴቶች ልጆቿ ትዕቢት፥ የምግብ ጥጋብ፥ የበለጸገ ምቾት ነበረ፥ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።


ሰውን ባያስጨንቅ፥ መያዣውን ባይወስድ፥ ባይቀማ፥ ከምግቡ ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቆተውንም በልብስ ቢሸፍን፥


ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፥ ዓይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፥ ደምንም ታፈስሳላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?


ምድር በደም ፍርድ ተሞልታለች፥ ከተማም በዓመፅ ተሞልታለችና፥ ሰንሰለት ሥራ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ ይህን አይተሃልን? በዚህ የሰሩትን ርኩሰት ሊያደርጉ ለይሁዳ ቤት ይህ ቀላል ነገር ነውን? ምድሪቱን በዓመፅ ሞልተዋታል፥ ሊያስቆጡኝም ተመልሰዋል፥ እነሆ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫቸው አቅርበዋል።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ ከመቅደሴ ሊያርቁኝ፥ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚፈጽሙትን ታላቅ ርኩሰት ታያለህን? ደግሞም ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኩሰት ታያለህ።


“ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን ጠብቅ፥ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።”


ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነው።


“እናንተ በሰማርያ ተራራ ያላችሁ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችግረኛውንም የምትጨቁኑ፥ ጌቶቻቸውንም፦ ‘አምጡ እንጠጣ’ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።


መበለቲቱንና ድኻ አደጉን፥ መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፤ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉ ነገር በልቡ አያስብ።


እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ፤ እናንተን የሚያስጨንቋችሁ ሀብታሞች አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤት የሚጐትቷችሁስ እነርሱ አይደሉምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos