ኢሳይያስ 25:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞትን ለዘለዓለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ ይህን ጌታ ተናግሮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞትንም ለዘላለም ይውጣል። ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤ የሕዝቡንም ውርደት ከምድር ሁሉ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሯልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር የሞትን ኀይል ለዘለዓለም ያጠፋል! ከሰዎችም ሁሉ ዐይን እንባን ያብሳል፤ ወገኖቹ በዓለም ሁሉ ላይ የተቀበሉትን ኀፍረት ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ራሱ ይህን ተናግሮአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞት ሰዎችን ዋጠ፤ በረታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር በአፉ ተናግሮአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞትን ለዘላለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፥ እግዚአብሔር ተናግሮአልና። |
ጌታም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።
ጌታም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፥ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላላም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
እነርሱም፦ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ብርታቱ የለም።
ጌታ የተቤዣቸው ይመለሳሉ ወደ ጽዮንም ይመጣሉ፤ የዘለዓለምም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ልቅሶም ይሸሻል።
በኀፍረታችሁ ፈንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፤ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፋንታችሁ ደስ ይለዋል፤ ስለዚህ የምድራቸውን ሁለት እጥፍ ይገዛሉ፥ የዘለዓለምም ደስታ ይሆንላቸዋል።
እናንት በቃሉ ፊት የምትርዱ፥ የጌታን ቃል ስሙ፦ የጠሉአችሁ የናንተው ሕዝብ፥ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ፦ “ደስታችሁን እንድናይ ጌታ ይክበር” ብለዋል፤ ነገር ግን ያፍራሉ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ድምፅሽን ከልቅሶ ዓይንሽንም ከእንባ ከልክዪ፤ ለሥራሽ የሚከፈልሽ ዋጋ ይሆናልና፥ ከጠላትም ምድር ይመለሳሉ፥ ይላል ጌታ።
ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ፥ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤ ሞት ሆይ! ቸነፈርህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! አጥፊነትህ ወዴት አለ? ርኅራኄ ከዓይኔ ተሰወረች።
አሁን ግን በወንጌል አማካይነት ሞትን በሻረው፥ ሕይወትንና ያለመበስበስን ወደ ብርሃን ባመጣው በአዳኛችን በክርስቶስ ኢየሱስ መገለጥ በኩል ተገለጠ።
እንባዎችንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ላይ ይጠርጋል፤ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና።”
በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”