Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 35:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፥ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላላም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ይመ​ለ​ሳሉ፤ በደ​ስ​ታም ተመ​ል​ሰው ወደ ጽዮን ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታም በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታ​ንም ያገ​ኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘ​ንና ትካ​ዜም ይጠ​ፋሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፥ የዘላላም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፥ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 35:10
31 Referencias Cruzadas  

እንባዎችንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ላይ ይጠርጋል፤ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና።”


በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖር ሕዝብ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅስም፤ በጩኸትም ድምፅ ይራራልሃል፥ በሰማህም ጊዜ ይመልስልሃል።


ሞትን ለዘለዓለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ ይህን ጌታ ተናግሮአል።


ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚያደርሰውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ ሳለ፥ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።


ራሱንም ለሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም ምስክርነት ተገቢ በሆነው በራሱ ጊዜ የቀረበ ነበር፤


እርሱም፦ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የሙሽራው ድምፅና የሙሽራይቱ ድምፅ፥ ወደ ጌታም ቤት፦ ‘ጌታ ቸር ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታን አመስግኑ!’ እያሉ የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ ነው። የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል ጌታ።


እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤት አደርጋለሁ በሕዝቤም ደስ ይለኛል፤ ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ አይሰማባትም።


እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደገና አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።


የሰው ልጅም ሊያገለግል፥ ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”


በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ ሲያልፉ የምንጭ ቦታ ያደርጉታል፥ የበልግም ዝናብ በረከትን ይሰጣልና።


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን፥ ሐዋርያትና ነቢያት ሆይ! ስለተፈረደባት በእርሷ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


ጌታ የዘለዓለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም፥ ጨረቃሽም አትገባም።


እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፥ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ።


ጌታ የታደጋቸው፥ ከጠላትም እጅ ያዳናቸው ይናገሩ።


በዕንባ የሚዘሩ በእልልታ ይለቅማሉ።


ጽዮን በፍትሕ፤ በንስሓ የሚመለሱ ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይዋጃሉ።


ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፤ የከበዳቸውን ቀንበር፤ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፤ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።


እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የጌታንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።


አንተ ትል ያዕቆብ፥ ታናሽ እስራኤል ሆይ፥ አትፍራ፤ እረዳሃለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።


ታበጥራቸዋለህ፥ ንፋስም ይጠርጋቸዋል፥ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል፤ አንተም በጌታ ደስ ይልሃል፥ በእስራኤልም ቅዱስ ትመካለህ።


ነገር ግን በፈጠርሁት ደስ ይበላችሁ ለዘለዓለምም ሐሤት አድርጉ፤ እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን ለሐሤት፥ ሕዝብዋንም ለደስታ እፈጥራለሁና።


ከእርሱም ዘንድ የምስጋናና የዘፋኞች የሐሤት ድምፅ ይወጣል፤ እኔም አበዛቸዋለሁ አያንሱምም፥ እኔም አስከብራቸዋለሁ ታናሽም አይሆኑም።


ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? ጌታ የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።


በዚያን ጊዜ አፋችን በሳቅ፥ አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፥ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ፦ ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ።


በኀፍረታችሁ ፈንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፤ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፋንታችሁ ደስ ይለዋል፤ ስለዚህ የምድራቸውን ሁለት እጥፍ ይገዛሉ፥ የዘለዓለምም ደስታ ይሆንላቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios