ኢሳይያስ 20:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት እንዲሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት በግብጽና በኢትዮጵያ ለምልክትና ለማስጠንቀቂያ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ ዕራቊቱን በባዶ እግሩ ሦስት ዓመት ሙሉ ሲመላለስ ነበር፤ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ የሚደርስባቸውም ምልክት ይኸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አለ፥ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት ራቁቱን በባዶ እግሩ እንደ ሄደ፥ እንዲሁ በግብፅና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ምልክትና ተአምራት ይደረጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አለ፦ ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥ |
የአሦርም ንጉሥ፦ “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊዋጋህ መጥቷል” የሚል ወሬ ሰማ። ይህን በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥ እንዲህም አለው፦
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ግብጽን የሚደግፉ ይወድቃሉ፥ የኃይልዋም ትዕቢት ይወርዳል፤ ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴቬኔ ድረስ በእርሷ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
የብረት ምጣድም ውሰድ፥ በአንተና በከተማይቱ መካከል የብረት ቅጥር አድርገው፥ ፊትህንም ወደ እርሷ አቅና፥ የተከበበችም ትሆናለች፥ አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።
ሊቀ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ! በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ ለሚመጣው ነገር ምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ! እነሆ፥ እኔ አገልጋዬን ቁጥቋጡን አወጣለሁ።
ምድሪቱን በሰላለችሁባት ቀን ቍጥር፥ አርባ ቀን፥ እያንዳንዱም ቀን እንደ አንድ ዓመት ሆኖ፥ በደላችሁን አርባ ዓመት ትሸከማላችሁ፥ መከፋቴንም ታውቃላችሁ።’