ሕዝቅኤል 18:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንንም ሰው ባያስጨንቅ፥ ነገር ግን ለባለ ዕዳው መያዣውን ቢመልስ፥ ባይቀማ፥ ከምግቡ ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቆተውንም በልብስ ቢሸፍን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንንም አይጨቍንም፤ ነገር ግን በመያዣ የወሰደውን እንኳ ለተበዳሪው ይመልሳል፤ ለተራበ የራሱን እንጀራ፣ ለተራቈተም ልብስ ይሰጣል እንጂ፣ በጕልበት አይቀማም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንንም አይጨቊንም፤ ነገር ግን በመያዣ የያዘውን ይመልሳል፤ አይቀማም፤ ለተራበ ያበላል፤ ለታረዘ ያለብሳል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውንም ባያስጨንቅ፥ ለባለ ዕዳም መያዣውን ቢመልስ፥ ፈጽሞም ባይቀማ፥ ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቈተውንም ከልብሱ ቢያለብስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውንም ባያስጨንቅ ለባለ ዕዳም መያዣውን ቢመልስ ፈጽሞም ባይቀማ ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ የተራቈተውንም በልብስ ቢያለብስ፥ |
በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በጭቆና የሚገኝ ትርፍን የሚጸየፍ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚሰበስብ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚከልል፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የወይን ቦታ የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም አትበድሉ፥ አታምፁባቸውም፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።
እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም በደል ይህ ነበር፤ በእርሷና በሴቶች ልጆቿ ትዕቢት፥ የምግብ ጥጋብ፥ የበለጸገ ምቾት ነበረ፥ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ጻድቁን ስለ ብር፥ ችግረኛውንም ስለ አንድ ጥንድ ጫማ ሸጠዋልና ስለ ሦስት የእስራኤል ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።