Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 25:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ለባልንጀራህም መሬት ብትሸጥ፥ ወይም ከባልንጀራህ እጅ ብትገዛ፥ አንዱ ሌላውን አያታልል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ ‘ከወገንህ ከአንዱ መሬት ብትገዛ ወይም ብትሸጥለት፣ አንዱ ሌላውን አያታልል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ ወገንህ ለሆነው እስራኤላዊ መሬት ብትሸጥ ወይም ከእርሱ መሬት ብትገዛ የግፍ ሥራ አትሥራ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህም አን​ዳች ብት​ሸ​ጥ​ለት፥ ወይም ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ እጅ ብት​ገዛ፥ ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን አያ​ስ​ጨ​ን​ቀው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ለባልንጀራህም አንዳች ብትሸጥለት፥ ወይም ከባልንጀራህ እጅ ብትገዛ፥ ሰው ባልንጀራውን አያታልል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 25:14
33 Referencias Cruzadas  

አሳም በባለ ራእዩ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በቊራኛ አስሮ በወህኒ ቤት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ፥ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አሠቃየ።


ፍርዱ ለወላጅ አልባና ለተጨቆነ ይደረግ ዘንድ፥ ሰዎች በምድር ላይ ማሸበራቸውን እንዳይቀጥሉ።


ድሀን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ይሰድባል፥ ለድሀ ምሕረትን የሚያደርግ ግን ያከብረዋል።


የድሀውን ጩኸት እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጮኻል አይሰማለትምም።


ለራሱ ጥቅም ሲል ድሀን የሚጐዳ፥ ለሀብታም የሚሰጥ፥ እርሱ ወደ ድህነት ይወድቃል።


አእምሮ የጐደለው መኰንን ትልቅ ግፈኛ ነው፥ ግፍን የሚጠላ ግን ብዙ ዘመን ይኖራል።


ድሆችን የሚያስጨንቅ ድሃ ሰው እህልን እንደሚያጠፋ እንደ ዶፍ ዝናብ ነው።


ሀብቱን በአራጣ ብዛትና በቅሚያ የሚያበዛ ለድሀ ለሚራራ ያከማችለታል።


በጠቅላላው ይህ ለአገሩ ይጠቅማል፤ ንጉሥም ከእርሻ ይጠቀማል።


መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን እሹ፤ የተገፉትን አጽናኑ፤ አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ ለመበለቶችም ተሟገቱ።


በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በጭቆና የሚገኝ ትርፍን የሚጸየፍ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚሰበስብ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚከልል፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የወይን ቦታ የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።


እኔስ የመረጥሁት ጾም፥ የበደልን እስራት እንድትፈቱ፥ የቀንበርንስ ጠፍር እንድትለቁ፥ የተገፉትን አርነት እንድታወጡ፥ ቀንበሩን ሁሉ እንድትሰብሩ አይደለምን?


ዓይንህና ልብህ ግን ለተጭበረበረ ትርፍ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ነው።”


አባትንና እናትን አቃለሉ፥ በመካከልሽ መጻተኛውን ጨቆኑ፥ በአንቺ ውስጥ የሙት ልጅንና መበለቲቱን አስጨነቁ።


“በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። ተቀጥሮ የሚያገለግለውን ሰው ደመወዙን እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አታቆይበት።


ከኢዮቤልዩ በኋላ እንደ ዓመታቱ ቍጥር ከባልንጀራህ ትገዛለህ፤ እርሱም እንደ መከሩ ዓመታት ቍጥር ይሸጥልሃል።


እኔም ጌታ አምላካችሁ ነኝና ሰው ባልንጀራውን አያታልል፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።


እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።


ወታደሮችም እንዲሁ፦ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ “ማንንም በግፍ ወይም በሐሰት ክስ አትበዝብዙ፤ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ፤” አላቸው።


ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ፤ ታታልሉማላችሁ፤ ያውም ወንድሞቻችሁን።


እርሱም ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎች ስለ ነበሩት እስራኤላውያንን ሃያ ዓመት እጅግ አስጨነቃቸው፤ እነርሱም ይረዳቸው ዘንድ ወደ ጌታ ጮኹ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos