Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 22:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የሚለብሰው ሌላ የለውም፥ ገላውን የሚሸፍንበት እርሱ ብቻ ነውና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ መሐሪ ነኝና እሰማዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 የጎረቤትህን ልብስ መያዣ አድርገህ ብትይዝ ሲመሽ መልስለት፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ልብሱን በመያዣ ስም የወሰድክበት ሰው ቢኖር ፀሐይ ከመጥለቅዋ በፊት መልስለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ልብስ ለመ​ያዣ ብት​ወ​ስድ ፀሐይ ሳት​ገባ መል​ስ​ለት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 የባልንጀራህን ልብስ ለመያዣ ብትወስድ ፀሐይ ሳትገባ መልስለት፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 22:26
16 Referencias Cruzadas  

ለማያውቀው ከተዋሰ ሰው ልብሱን ውሰድ፥ ለእንግዳ የተዋሰውንም እርሱን አግተው።


በመሠዊያውም ሁሉ አጠገብ ለመያዣነት በተወሰደው ልብስ ላይ ይተኛሉ፤ በአምላካቸውም ቤት ውስጥ በካሣ የተወሰደውን ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።


“ወፍጮና መጁን ወይም መጁንም ቢሆን፥ የብድር መያዣ አድርገህ አትውሰድ፤ የሰውን ነፍስ መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆናልና።


ሰውን ባያስጨንቅ፥ መያዣውን ባይወስድ፥ ባይቀማ፥ ከምግቡ ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቆተውንም በልብስ ቢሸፍን፥


ማንንም ሰው ባያስጨንቅ፥ ነገር ግን ለባለ ዕዳው መያዣውን ቢመልስ፥ ባይቀማ፥ ከምግቡ ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቆተውንም በልብስ ቢሸፍን፥


መክፈል ባትችል፥ ለምን የምትተኛበት አልጋ ይወሰድብሃል?


የወላጅ አልባውን አህያ ይነዳሉ፥ የመበለቲቱን በሬ ለመያዣነት ይወስዳሉ።


“ለመጻተኛው ወይም አባት ለሌለው ልጅ ፍትሕ አትንፈገው፤ የመበለቲቱንም መደረቢያ መያዣ አታድርግ።


ኃጢአተኛውም መያዣን ቢመልስ፥ የነጠቀውንም ቢመልስ፥ በሕይወትም ትእዛዝ ቢሄድ ኃጢአትም ባይሠራ፥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።


አባቱ የሞተበትን ልጅ ከጡቱ የሚነጥሉ አሉ፥ ከችግረኛውም መያዣ ይወስዳሉ።


ከወንድሞችህ አላግባብ መያዣ ወስደሃል፥ የታረዙትንም ልብስ ዘርፈሃል።


ራቁታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፥ በብርድ ጊዜ የሚደረብ የላቸውም።


አየኸው፥ አንተ ክፋትንና ቁጣን ትመለከታለህና በእጅህ ፍዳውን ለመስጠት፥ ምስኪን እራሱን ለአንተ አሳልፎ ይሰጣል፥ ለድሀ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።


ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ ጌታም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios