አቤቱ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ ‘እኔ ለአንተ ቤት እሠራልሃለሁ’ ብለህ ይህን ለአገልጋይህ ገልጸህለታል። ስለዚህ አገልጋይህ ይህችን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ ድፍረት አግኝቶአል።
ዘፀአት 35:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቡ ያነሣሣውና መንፈሱ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ ሰው ሁሉ ለመገናኛው ድንኳን ሥራና ለአገልግሎቱ ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ የሚሆን ለጌታ ስጦታ አመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈቃደኛ የነበረና ልቡን ያነሣሣው ሁሉ በመምጣት ለመገናኛው ድንኳን ሥራ፣ ለአገልግሎቱ ሁሉና ለተቀደሱ ልብሶች የሚሆን ለእግዚአብሔር መባ አመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሥራት እያንዳንዱ ለመስጠት ልቡ የፈቀደውን ለእግዚአብሔር መባ አመጣ፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን ለመንፈሳዊ አገልግሎት ለካህናት ልብስ የሚሆነውን ነገር ሁሉ አመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ሰው ሁሉ እያንዳንዱ ልቡ እንዳነሣሣው፥ መንፈሱም እሺ እንዳሰኘው ለምስክሩ ድንኳን ሥራ ለማገልገያውም ሁሉ ለመቅደስ ልብስ ለእግዚአብሔር ስጦታ አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ሰው ሁሉ ልቡ እንዳነሣሣው መንፈሱም እሺ እንዳሰኘው ለመገናኛው ድንኳን ሥራ ለማገልገያውም ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ ለእግዚአብሔር ስጦታ አመጡ። |
አቤቱ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ ‘እኔ ለአንተ ቤት እሠራልሃለሁ’ ብለህ ይህን ለአገልጋይህ ገልጸህለታል። ስለዚህ አገልጋይህ ይህችን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ ድፍረት አግኝቶአል።
ንጉሡም ዳዊት ተነሥቶ በመቆም እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ! ስሙኝ፤ ለጌታ ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የሚሆን የማረፍያ ቤት ለመሥራት እኔ በልቤ አስቤያለሁ፤ ለግንባታም የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ፤
“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።
ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል በፈቃደኝነት ልናቀርብልህ የምንችል እኔ ማን ነኝ? ሕዝቤስ ማን ነው?
ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን ቤት ስለወደድሁ፥ ለመቅደሱ ካዘጋጀሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ።
ከአባቶች ቤቶች አለቆች አንዳንዶች፥ በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ጌታ ቤት በመጡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው እንዲሠራ በፈቃዳቸው መባ ሰጡ።
ልባቸው የተነሣሣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ የአፍንጫ ጌጦችን፥ ሎቲዎችን፥ ቀለበቶችን፥ ድሪዎችን፥ የወርቅ ጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሰዎች ሁሉ የወርቅ ስጦታ ለጌታ አመጡ።
ከእስራኤል ልጆች ልባቸው ያነሣሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጌታ በሙሴ እጅ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ሁሉ የሚሆን ስጦታ በፈቃዳቸው ለጌታ አመጡ።
አለቃቸው ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ይሆናል፥ ገዥአቸውም ከመካከላቸው ይወጣል፤ እኔ አቀርበዋለሁ እርሱም ይቀርበኛል፤ ይህስ ባይሆን ለነፍሱ ዋስትና ሰጥቶ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው? ይላል ጌታ።