Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 4:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ከሁሉ አስበልጠህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት ምንጭ እርሱ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ልብ የሕይወት ምንጭ ስለ ሆነ ልብህን ከሁሉ ነገር አስበልጠህ ጠብቀው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ልብህን አጥብቀህ ጠብቅ፥ የሕይወት መገኛ ከእርሱ ነውና።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 4:23
21 Referencias Cruzadas  

መልካም ሰው በልቡ ከሚገኘው መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ከሚገኘው ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል፤ በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና።


አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋት ያገኘዋል።


የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?


ከልብ ክፉ ሐሳብ፥ መግደል፥ ማመንዘር፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።


ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ጠቢብም ሁን፥ ልብህንም በቀናው መንገድ ምራ።


በገዛ ልቡ የሚታመን ሰው ሞኝ ነው፥ በጥበብ የሚመላለስ ግን ይድናል።


ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ፤ ጸልዩም፤ መንፈስ ዝግጁ ነው፥ ሥጋ ግን ደካማ ነው።”


“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።


ከመካከላችሁ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት መራራ ሥር በቅሎ እንዳያስጨንቃችሁ፥


የጥበብ መጀመሪያ እነሆ፥ ጥበብን አግኝ፥ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።


ልጄ ሆይ፥ እነዚህ ከዐይኖችህ አይራቁ፥ መልካም ጥበብንና ጥንቃቄን ጠብቅ።


እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ላይ ይገኛሉ፥ ነፍሱን ግን የሚጠብቅ ከእነርሱ ይርቃል።


ሞገስ ያላት ሴት ክብርን ታገኛለች፥ ኃያላንም ሀብትን ያገኛሉ።።


ያችም ሀብት በክፉ ነገር ትጠፋለች፥ ልጅንም ቢወልድ በእጁ ምንም የለውም።


ከአፍ የሚወጣው ግን ከልብ ይወጣል፤ እነዚህ ሰውን ያረክሱታል።


ኢዩ ግን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ታዛዥ ሆኖ አልተገኘም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራቸውን የኢዮርብዓምን ክፉ አርአያነት ተከተለ።


የቅኖች መንገድ ከክፋት መራቅ ነው፥ መንገዱን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios