Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 29:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና፥ በፍጹም ልባቸውም ለጌታ በፈቃዳቸው አቅርበዋልና ደስ አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ደግሞ ፍጹም ደስ ተሰኘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ስጦታው በገዛ ፈቃድና በፍጹም ልብ የቀረበ በመሆኑ፣ አለቆቹ ለእግዚአብሔር ስላደረጉት የበጎ ፈቃድ ስጦታ ሕዝቡ ደስ አለው፤ ንጉሥ ዳዊትም እንደዚሁ እጅግ ደስ አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሕዝቡ በፈቃዳቸውና በሙሉ ልብ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰጡ፤ እጅግ ብዙ ሀብት ገቢ በመሆኑም ደስ አላቸው፤ ንጉሥ ዳዊትም ከመጠን በላይ ደስ ተሰኘ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሕዝ​ቡም ፈቅ​ደው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፥ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አቅ​ር​በ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና፥ በፍጹም ልባቸውም ለእግዚአብሔር በፈቃዳቸው አቅርበዋልና ደስ አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ደግሞ በታላቅ ደስታ ደስ አለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 29:9
22 Referencias Cruzadas  

እንደ ዐቅማቸው መጠን፥ ዐቅማቸውም የሚያልፍ እንኳን፥ ወደው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁ።


በዛሬው ቀን እንዳደረጋችሁት በድንጋጌው ትኖሩና ትእዛዞቹንም ታከብሩ ዘንድ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ታማኞች ሁኑ።”


ነገር ግን አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደገና ማሰብ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ተሰኝቻለሁ፤ አጋጣሚዎች አልተመቻቹላችሁም እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር።


ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን፥ ደስታችሁም ፍጹም እንዲሆን ይህን ነግሬአችኋለሁ።


አምላኬ ሆይ! ልብን እንደምትመረምር፥ ቅንነትንም እንደምትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱና ደስ ተሰኝቶ እንዳቀረበልህ አይቻለሁ።


ስለዚህ የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ደስታዬና አክሊሌ ናችሁ፤ የተወደዳችሁ ሆይ! በዚህ መንገድ በጌታ ጸንታችሁ ቁሙ።


በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ ባለው ባለው መጠን ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ የሌላውን አይጠበቅበትም።


ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ ‘የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ፤’ ይላቸዋል።


ግርማዊ ክብር ከልደትህ ጊዜ አንሥቶ፥ የተቀደሰ ሞገስም ከማኅጸን፥ የወጣትነትም ጠል የአንተ ነው።


ልቤ ወደ እስራኤል አለቆች ነው፥ በሕዝቡ መካከል ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ወደ ሰጡት፥ ጌታን አመስግኑ።


ከእስራኤል ልጆች ልባቸው ያነሣሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጌታ በሙሴ እጅ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ሁሉ የሚሆን ስጦታ በፈቃዳቸው ለጌታ አመጡ።


ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት ጌታን ባረከ፤ ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “አቤቱ፥ የአባታችን የእስራኤል አምላክ ሆይ! ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ተባረክ።


ከእርሱም በኋላ በፈቃዱ ራሱን ለጌታ የቀደሰ የዝክሪ ልጅ ዓማስያ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ።


እያንዳንዱ ካህን ከሚያገለግላቸው ሰዎች የሚገኘውን የገንዘብ መባ ሁሉ በጥንቃቄ የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጠው፤ ገንዘቡንም እንዳስፈላጊነቱ ለቤተ መቅደሱ ጥገና አገልግሎት እንዲያውሉት ነገራቸው።


አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ደስ ብሎአቸው ግብሩን አመጡ፥ እስኪሞላም ድረስ በሣጥኑ ውስጥ ጣሉት።


ሕዝቅያስና ሹማምንቱም መጥተው ክምሩን ባዩ ጊዜ ጌታንና ሕዝቡን እስራኤልን ባረኩ።


በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት መባ ሁሉ በተጨማሪ በእጃቸው፥ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በዕቃዎችና በእንስሶችና በውድ ነገሮች አበረታቱአቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios