Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፥ ባራቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ‘ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ቅኔም ተቀኚ፤ የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ሆይ፤ ተነሣ፤ ምርኮኞችህንም ማርከህ ውሰድ’ አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዲቦራ ሆይ! ንቂ! ንቂ! ንቂ! መዝሙርም ዘምሪ! የአቢኒዔም ልጅ ባራቅ ሆይ! ተነሣ! ምርኮህንም እየመራህ ወደ ፊት ገሥግሥ!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ተነሺ፥ ዲቦራ ሆይ፦ ተነሺ፤ አእ​ላ​ፍን ከሕ​ዝብ ጋር አስ​ነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቅኔ​ው​ንም ተቀኚ፤ ባርቅ ሆይ! በኀ​ይል ተነሣ፤ ዲቦ​ራም ባር​ቅን አጽ​ኚው፥ የአ​ቢ​ኒ​ሔም ልጅ ባር​ቅም ሆይ! ምር​ኮ​ህን ማርክ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፥ ባርቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 5:12
18 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ “ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ፤ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ፤” ይላል።


የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሺህ ናቸው፥ ጌታ በመቅደሱ በሲና በመካከላቸው ነው።


ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑ ነው፥ እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ።


እንዲሁም ፈቃዱን ለመፈጸም ታስረው ከተያዙበት ከዲያብሎስ ወጥመድ ወጥተው ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ ያደርጋቸዋልና።


የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ስለዚህ “አንተ የምታንቀላፋ ንቃ፤ ከሙታንም ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል፤” ተብሏል።


ወደ ሰከነ ልቦናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና ይህንንም የምለው ላሳፍራችሁ ነው።


ከዚህም በኋላ ነቃሁ ተመለከትሁም፥ እንቅልፌም ጣፋጭ ሆነልኝ።


ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የጌታም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ።


ከጌታ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ! ቁሚ፤ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል ጨልጠሽውማል።


የጌታ ክንድ ሆይ! ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?


አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፥ አንተም ሳትካድ ክህደትን የምትፈጽም ወዮልህ! ማጥፋትን በተውክ ጊዜ ትጠፋለህ፤ መካድን በተውክ ጊዜ ትካዳለህ።


አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል፥ የእስራኤልም ቤት በእግዚአብሔር ምድር እንደ ሎሌዎችና እንደ ገረዶች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ የማረኩአቸውን ይማርካሉ፥ አስጨናቂዎችንም ይገዛሉ።


አምላኬ ሆይ ልቤ ጽኑ ነው፥ እቀኛለሁ፥ በክብሬም እዘምራለሁ።


በዚያ ጊዜ የቀሩት ወደ ኃያላኑና ወደ ሕዝቡ ወረዱ፥ ጌታም ስለ እኔ በኃያላን ላይ ወረደ።


ክብሬ ይነሣ፥ በገናና መሰንቆም ይነሡ፥ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios