ዘፀአት 12:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ ምድር አልፋለሁ፥ በግብጽም ምድር ከሰው እስከ ከብት ድረስ በኩርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብጽም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ ምድር ላይ ዐልፋለሁ፤ ከሰውም ከእንስሳም የተወለደውን የበኵር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽን አማልክት ሁሉ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚያችም ሌሊት እኔ በግብጽ ምድር ሁሉ እየተላለፍኩ እያንዳንዱን የሰውም ሆነ የእንስሳ ዘር የሆነውን የበኲር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽንም አማልክት ሁሉ እቀጣለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ ሀገር አልፋለሁ፤ በግብፅም ሀገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ በቀልን አደርግባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፤ በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
ጌታ ግብጽን ሊመታ ያልፋል፤ ደሙንም በጉበኖቹና በሁለቱ መቃኖች ላይ ያያል፥ ጌታም በበሩ ያልፋል፥ አጥፊውም ሊመታችሁ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይፈቅድም።
ስለ ግብጽ የተነገረ ትንቢት። እነሆ፥ ጌታ በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።
በግብጽም አማልክት ቤቶች እሳትን አነድዳለሁ፤ የባቢሎንም ንጉሥ ያቃጥላቸዋል ይማርካቸዋልም፤ እረኛም ደበሎውን እንደሚደርብ እንዲሁ የግብጽን አገር ይደርባል፤ ከዚያም ስፍራ በሰላም ይወጣል።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ የኖእ አሞንን፥ ፈርዖንንም፥ ግብጽንም፥ አማልክቶችዋንና ነገሥታቶችዋንም፥ ፈርዖንና በእርሱም የሚታመኑትን እቀጣለሁ፤
በሚሄዱባቸው አሕዛብ መካከል ርኩሰታቸውን ሁሉ እንዲናገሩ ከእነርሱ ጥቂቶች ከሰይፍ፥ ከራብና ከቸነፈር አስቀራለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
ጌታ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርን አማልክት ሁሉ ያጠፋቸዋልና፤ የሕዝቦችም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች፥ ሁሉም በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።
የአሽዶድም ሰዎች በማግስቱ ማለዳ ተነሥተው ሲመለከቱ እነሆ፥ ዳጎን በጌታ ታቦት ፊት መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት። ከዚያም አንሥተው ዳጎንን ወደ ቦታው መለሱት።
አገሩን በማጥፋት ላይ ባሉት ዕባጮችና ዐይጦች ዓይነት ምስሎችን ሠርታችሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ክብር ስጡ። ይህን ካደረጋችሁ እጁን ከእናንተ፥ ከአማልክቶቻችሁና ከምድራችሁ ላይ ያነሣ ይሆናል።