Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 14:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አማልክቶቻቸውንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊትም አዘዘ፥ በእሳትም አቃጠሉአቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ፍልስጥኤማውያን አማልክታቸውን በዚያው ጥለዋቸው ስለ ነበር፣ ዳዊት በእሳት እንዲያቃጥሏቸው አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ፍልስጥኤማውያን ሲሸሹ ጣዖቶቻቸውን ጥለው ሄዱ፤ ዳዊትም ጣዖቶቹ በሙሉ እንዲቃጠሉ ትእዛዝ ሰጠ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊ​ትም፥ “በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸው” ብሎ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አማልክቶቻቸውንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊትም አዘዘ፤ በእሳትም አቃጠሉአቸው።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 14:12
10 Referencias Cruzadas  

የሠሩትን ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እስኪደቅም ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲጠጡት አደረገ።


ከእንጨትና ከድንጋይ ተጠርበው የተሠሩ የሰው እጅ ሥራ እንጂ አማልክት ስላልነበሩ በእሳት ላይ ጥለው አጠፉአቸው።


የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ አትመኝ፥ በጌታ አምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።


ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም አድቅቁት፥ የእነርሱንም አሼራ ሰባብሩ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ።


እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ ምድር አልፋለሁ፥ በግብጽም ምድር ከሰው እስከ ከብት ድረስ በኩርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብጽም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


ፍልስጥኤማውያንም ጣዖቶቻቸውን ትተው ሸሹ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ወሰዱአቸው።


ወደ በኣል-ፐራሲምም ወጡ፥ በዚያም ዳዊት ድል ነሣቸው። ዳዊትም፦ “ግድቡን አፍርሶ እንደሚወጣ ጎርፍ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣል-ፐራሲም ብለው ጠሩት።


ዳግመኛም ፍልስጥኤማውያን በሸለቆው አደጋ ጣሉ።


በዚያ ያመልኩት የነበረውን የድንጋይ ዐምድ ወደ ውጪ አውጥተው በእሳት አቃጠሉት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios