እንዲህም አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን በአፉ እንደ ተናገረ፥ በእጁም ፈጽሙአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፦
1 ጴጥሮስ 1:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ ከምሕረቱ ብዛት በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይመስገን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ እርሱ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ምክንያት ለሕያው ተስፋ በሚሆን አዲስ ልደት፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኀይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል። |
እንዲህም አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን በአፉ እንደ ተናገረ፥ በእጁም ፈጽሙአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፦
ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ “አምላካችሁን ጌታን ባርኩ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለጌታና ለንጉሡ ሰገዱ።
ወደ ጌታ ጸለየ፥ እንዲህም አለ፦ “ጌታ ሆይ፥ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አስቀድሜ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል የፈለግሁትም ለዚህ ነበር፥ አንተ ቸርና ርኅሩኅ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ ከክፉ የምትመለስ አምላክ እንደሆንህ አውቄ ነበርና።
ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፥ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ፥ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈሱ አማካይነት፥ ለሟች አካላቶቻችሁ ሕይወትን ይሰጠዋል።
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት የምትጸኑ ከሆነ ነው፤ ይህም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፤ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።
ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለጠግነት ምን እንደሆነ ሊያሳውቅ ወደደ፤ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ያለው ክርስቶስ ነው።
በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት የእምነታችሁን ሥራ፥ የፍቅራችሁን ድካም፥ በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን የተስፋችሁንም መጽናት እናስታውሳለን።
ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! አንቀላፍተው ስላሉት፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ሰዎች ደግሞ ልታዝኑ እንደማይገባ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።
እንዲሁም የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እንድንጠብቅ ያስተምረናል፤
ነገር ግን ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተም ስላለች ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤
ይህ ውሃ አሁን የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ እናንተን ያድናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ ሳይሆን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የበጎ ሕሊና ልመና ነው።
ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚያፈቅር ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፥ እግዚአብሔርንም ያውቃል።
ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንደማያደርግ እናውቃለን፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን ይጠብቃል፤ ክፉውም አይነካውም።