Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዮናስ 4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


የዮናስ ብስጭት

1 ይህም ዮናስን ከቶ ደስ አላሰኘውም፥ ክፉኛም አበሳጨው።

2 ወደ ጌታ ጸለየ፥ እንዲህም አለ፦ “ጌታ ሆይ፥ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አስቀድሜ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል የፈለግሁትም ለዚህ ነበር፥ አንተ ቸርና ርኅሩኅ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ ከክፉ የምትመለስ አምላክ እንደሆንህ አውቄ ነበርና።

3 አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ከሕይወት ሞት ይሻላልና፥ እባክህ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ።”

4 ጌታም፦ “አንተ ልትቆጣ ተገቢ ነውን?” አለ።

5 ዮናስም ከከተማይቱ ወጣ፥ ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ፥ ከተማይቱ የሚደርስባትን እስኪያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠራ፥ ከጥላዋ በታችም ተቀመጠ።

6 ጌታ እግዚአብሔርም የጉሎ ተክል አበቀለ፥ ከጭንቀቱም እንድታድነው፥ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ እንድትል አደረጋት፤ ዮናስም ስለ ጉሎ ተክሉ እጅግ ተደሰተ።

7 በማግስቱ ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ትልን አዘጋጀ፥ እርሷም የጉሎውን ተክል መታች፤ ደረቀም።

8 ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።


የዮናስ ክርክር

9 እግዚአብሔርም ዮናስን “ስለዚች የጉሎ ተክል ልትቆጣ ይገባህልን?” አለው። እርሱም፦ “እስከ ሞት ድረስ ልቆጣ ይገባኛል” አለ።

10 ጌታም እንዲህ አለው፦ “አንተ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፥ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው የጉሎ ተክል አዝነሃል።

11 እኔስ ታዲያ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos