Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 8:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እንዲህም አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን በአፉ እንደ ተናገረ፥ በእጁም ፈጽሙአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚያም እንዲህ አለ፤ “ለአባቴ ለዳዊት በገዛ አፉ ተናግሮ የሰጠውን ተስፋ፣ እርሱ ራሱ በእጁ የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እርሱም እንዲህ ብሎ ነበርና፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን አጽንቶ ጠብቆአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፦

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እር​ሱም አለ፥ “ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት በአፉ የተ​ና​ገረ፥ በእ​ጁም የፈ​ጸመ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15-16 እርሱም አለ “‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ፥ በእርስዋም ቤት ይሠራልኝ ዘንድ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከተማ አልመረጥሁም፤ አሁን ግን ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይሆን ዘንድ ዳዊትን መርጫለሁ፤’ ብሎ ለአባቴ ለዳዊት በአፉ የተናገረ፥ በእጁም የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 8:15
29 Referencias Cruzadas  

“የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፤ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤


ሌዋውያኑ ኢያሱ፥ ቃድምኤል፥ ባኒ፥ ሐሻብንያ፥ ሼሬብያ፥ ሆዲያ፥ ሽባንያ፥ ፕታሕያ እንዲህ አሉ፦ “ቁሙ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ጌታ አምላካችሁን ባርኩ። ከበረከትና ከምስጋና ሁሉ በላይ ከፍ ያለው የክብርህን ስም ይባርኩ።


ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ “አምላካችሁን ጌታን ባርኩ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለጌታና ለንጉሡ ሰገዱ።


ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት ጌታን ባረከ፤ ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “አቤቱ፥ የአባታችን የእስራኤል አምላክ ሆይ! ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ተባረክ።


ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረ፤


እኛ ሕያዋን ግን ከአሁን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ጌታን እንባርካለን። ሃሌ ሉያ።


እርሱም እንዲህ አለ፦ “ለአባቴ ለዳዊት እንዲህ ብሎ በአፉ የተናገረው በእጁም የፈፀመው የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ፤ እርሱም እንዲህ አለው፦


ጌታ ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።


ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ ከምሕረቱ ብዛት በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይመስገን፤


በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በሰማያዊ ስፍራ በክርስቶስ የባረከን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ።


እንዲሁም ለአባቶቻችን ምሕረትን አደረገ፤ ቅዱስ ኪዳኑንም


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


እምቢ ብላችሁ ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችኋል።” የጌታ አፍ ይህን ተናግሮአልና።


ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፥ ስለ ጽኑ ፍቅርሀና ስለ ታማኝነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህንና ቃልህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።


እኔንም ስለ ቅንነቴ ደገፍከኝ፥ በፊትህም ለዘለዓለም አጸናኸኝ።


በአራተኛውም ቀን በበረከት ሸለቆ ውስጥ ተሰበሰቡ፥ በዚያም ጌታን ባረኩ፤ ስለዚህም ያ ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የበረከት ሸለቆ ተባለ።


እርሱ ቤት ይሠራልኛል፤ ዙፋኑንም ለዘለዓለም አጸናለሁ።


አሁንም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአገልጋይህና ለቤቱ የሰጠኸውን ተስፋ ለዘለዓለም ጠብቅለት፤ እንደተናገርኸውም ፈጽም፤


“ሂድና አገልጋዬን ዳዊትን፥ ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ የምኖርበትን ቤተ መቅደስ የምትሠራልኝ አንተ ነህን?’


ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ ሕዝቡን በሠራዊት ጌታ ስም ባረከ።


ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ።” ሕዝቡም ሁሉ “አሜን” አሉ፤ ጌታንም አመሰገኑ።


እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፥ ልጅም ይሆነኛል፥ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ የመንግሥቱንም ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጸናለሁ።’


ዳዊትም አቢጌልን እንዲህ አላት፤ “ዛሬ እንድታገኚኝ ወደ እኔ የላከሽ፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ የተመሰገነ ይሁን!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios