ሆሴዕ 8:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፋስን ዘርተዋልና ዐውሎ ነፋስን አጨዱ፤ ለነዶአቸውም ኀይል የለውም፤ ከፍሬውም ዱቄት አይገኝም፤ ቢገኝም ጠላት ይበላዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነፋስን ይዘራሉ፤ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤ አገዳው ዛላ የለውም፤ ዱቄትም አይገኝበትም፤ እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ ባዕዳን ይበሉታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፋስን ዘሩ፥ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤ የቆመውም እህል ዛላ የለውም፥ ከእርሱም ዱቄት አይገኝም፤ ቢገኝም እንኳ ባዕዳን ይበሉታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ነፋስን ዘርቶ ዐውሎ ነፋስን እንደሚያጭድ ይሆናሉ፤ ዛላ የሌለው የእህል አገዳ ምግብ ሊሆን አይችልም፤ ፍሬ ቢኖረውም እንኳ የሚበሉት ባዕዳን በሆኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፋስን ዘርተዋል፥ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፥ አገዳ የለውም፥ ከፍሬውም ዱቄት አይገኝም፥ ቢገኝም እንግዶች ይበሉታል። |
በዘመኑም የአሶር ንጉሥ ፎሐ በምድሪቱ ላይ ወጣ፤ ምናሔምም የፎሐ እጅ ከእርሱ ጋር እንዲሆን አንድ ሺህ መክሊት ብር ሰጠው።
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የሥራውንም መቅሠፍት ይፈጽማል። እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚሰጥ ሰውን ይወድዳል፥ ከንቱ ሥራውን ግን ይጠላል።
ተክልን በተከልህበት ቀን ትበድላለህ፤ የዘራኸውም በበነጋው በምታወርስበት ቀን ይበቅላል፤ አባትም ለልጁ እንደሚያወርስ አንተም ለልጆችህ ታወርሳለህ።
ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፤ በረከትንም ብሉ፤ ሰውነታችሁም በበረከት ደስ ይበለው።
እነሆ፥ እግዚአብሔር መዓቱን በቍጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ እንደ እሳት ይመጣል፤ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።
ስንዴን ትዘራላችሁ፤ እሾህንም ታጭዳላችሁ፤ ዕጣችሁም ምንም አይጠቅማችሁም፤ ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ በአዝመራችሁ ታፍራላችሁ።
ስለዚህ እህሌን በጊዜው፥ ወይኔንም በወራቱ እወስዳለሁ፤ ኀፍረቷንም እንዳትሸፍን ልብሴንና መጎናጸፊያዬን እገፍፋታለሁ።
ኤፍሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ፍሬ አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ የተወደደውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።
እግዚአብሔር ትዕግሥተኛ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፣ እግዚአብሔር በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።
ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፣ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፣ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፣ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፣ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ።
የምድርህን ፍሬ፥ ድካምህንም ሁሉ የማታውቀው ሕዝብ ይበላዋል፤ አንተም ሁልጊዜ የተጨነቅህ፥ የተገፋህም ትሆናለህ።