Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ጠላት ጕል​በ​ቱን በላው፤ እርሱ ግን አላ​ወ​ቀም፤ ሽበ​ትም ወጣ​በት፤ እር​ሱም ገና አላ​ስ​ተ​ዋ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እንግዶች ጕልበቱን በዘበዙ፤ እርሱ ግን አላስተዋለም። ጠጕሩም ሽበት አወጣ፤ እርሱ ግን ልብ አላለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ባዕዳን ጉልበቱን በዘበዙ፥ እርሱም አላወቀም፤ ሽበትም ወጣበት፥ እርሱም አላወቀም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ባዕዳን ጒልበታቸውን በዘበዙት፤ እነርሱ ግን አልተገነዘቡትም፤ ሽበት ጣል ጣል አድርጎባቸዋል፤ እነርሱ ግን አልተገነዘቡትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እንግዶች ጕልበቱን በሉት፥ እርሱም አላወቀም፥ ሽበትም ወጣበት፥ እርሱም አላወቀም።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 7:9
10 Referencias Cruzadas  

አዛ​ሄ​ልም በኢ​ዮ​አ​ካዝ ዘመን ሁሉ እስ​ራ​ኤ​ልን አስ​ጨ​ነቀ፤


በዘ​መ​ኑም የአ​ሶር ንጉሥ ፎሐ በም​ድ​ሪቱ ላይ ወጣ፤ ምና​ሔ​ምም የፎሐ እጅ ከእ​ርሱ ጋር እን​ዲ​ሆን አንድ ሺህ መክ​ሊት ብር ሰጠው።


“መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም፤ ዘበቱብኝ፥ እኔም አላወቅሁም። ከእኔ ጋር የሚሄዱትን መጥቼ እፈልግ ዘንድ መቼ ጧት ይሆናል?” ትላለህ።


ምድ​ራ​ችሁ ባድማ ናት፤ ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ሳት ተቃ​ጠሉ፤ እር​ሻ​ች​ሁ​ንም በፊ​ታ​ችሁ ባዕ​ዳን ይበ​ሉ​ታል፤ ጠላ​ትም ያጠ​ፋ​ዋል፤ ባድ​ማም ያደ​ር​ገ​ዋል።


አላ​ወ​ቅ​ህም፤ አላ​ስ​ተ​ዋ​ል​ህም፤ ጆሮ​ህን ከጥ​ንት አል​ከ​ፈ​ት​ሁ​ል​ህም፤ አንተ ፈጽሞ ወን​ጀ​ለኛ እንደ ሆንህ፥ ከማ​ኅ​ፀ​ንም ጀም​ረህ ተላ​ላፊ ተብ​ለህ እንደ ተጠ​ራህ ዐው​ቄ​አ​ለ​ሁና።


ጻድቅ ሰው እን​ደ​ጠፋ አያ​ችሁ፤ ይህ​ንም በል​ባ​ችሁ አላ​ሰ​ባ​ች​ሁም፤ ጻድ​ቃን ሰዎች ይወ​ገ​ዳሉ፤ ጻድ​ቅም ከክ​ፋት ፊት እንደ ተወ​ገደ ማንም አያ​ስ​ተ​ው​ልም።


ሕዝቤ አእ​ምሮ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ይመ​ስ​ላሉ፤ አን​ተም አእ​ም​ሮህ ተለ​ይ​ቶ​ሃ​ልና እኔ ካህን እን​ዳ​ት​ሆ​ነኝ እተ​ው​ሃ​ለሁ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ ረስ​ተ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ልጆ​ች​ህን እረ​ሳ​ለሁ።


ነፋ​ስን ዘር​ተ​ዋ​ልና ዐውሎ ነፋ​ስን አጨዱ፤ ለነ​ዶ​አ​ቸ​ውም ኀይል የለ​ውም፤ ከፍ​ሬ​ውም ዱቄት አይ​ገ​ኝም፤ ቢገ​ኝም ጠላት ይበ​ላ​ዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos