La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 21:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዕብ​ራዊ ባሪያ የገ​ዛህ እንደ ሆነ ስድ​ስት ዓመት ያገ​ል​ግ​ልህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት በነጻ አር​ነት ይውጣ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ዕብራዊ አገልጋይ ብትገዛ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፤ በሰባተኛው ዓመት ግን ያለ ምንም ክፍያ በነጻ ይሂድ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዕብራዊ ባርያ የገዛህ እንደሆነ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፥ በሰባተኛው ዓመት ግን እንዲሁ ነፃ ይውጣ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዕብራዊ ባሪያ ብትገዛ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፤ በሰባተኛው ዓመት ያለ ምንም ዕዳ ነጻ እንዲወጣ አድርገው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዕብራዊ ባሪያ የገዛህ እንደሆነ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፥ በሰባተኛውም በከንቱ አርነት ይውጣ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 21:2
18 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ማይ ጠል፥ ከም​ድ​ርም ስብ፥ የእ​ህ​ል​ንም፥ የወ​ይ​ን​ንም፥ የዘ​ይ​ት​ንም ብዛት ይስ​ጥህ፤


ዔሳ​ውም አለ፥ “በእ​ው​ነት ስሙ ያዕ​ቆብ ተባለ፤ ሁለት ጊዜ አሰ​ና​ክ​ሎ​ኛ​ልና፤ መጀ​መ​ሪያ ብኵ​ር​ና​ዬን ወሰደ፤ አሁ​ንም እነሆ በረ​ከ​ቴን ወሰደ።” ዔሳ​ውም አባ​ቱን አለው፥ “ደግ​ሞም አባቴ ሆይ፥ ለእኔ በረ​ከ​ትን አላ​ስ​ቀ​ረ​ህ​ል​ኝ​ምን?”


ከነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች የአ​ንዱ ሚስት የሆ​ነች አን​ዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪ​ያህ ሞቶ​አል፤ ባሪ​ያ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆ​ቼን ባሪ​ያ​ዎች አድ​ርጎ ሊወ​ስ​ዳ​ቸው መጥ​ቶ​አል” ብላ ወደ ኤል​ሳዕ ጮኸች።


እኔም፥ “ለአ​ሕ​ዛብ የተ​ሸ​ጡ​ትን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንን አይ​ሁ​ድን በፈ​ቃ​ዳ​ችን ተቤ​ዠን፤ እና​ን​ተስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ትሸ​ጣ​ላ​ች​ሁን? እነ​ር​ሱስ ለእኛ የተ​ሸጡ ይሆ​ና​ሉን?” አል​ኋ​ቸው። እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ መል​ስም አላ​ገ​ኙም።


አገ​ል​ጋይ ወይም በብር የተ​ገዛ ቢኖር ከተ​ገ​ረዘ በኋላ ያን ጊዜ ከእ​ርሱ ይብላ።


ብቻ​ውን መጥቶ እንደ ሆነ ብቻ​ውን ይውጣ፤ ከሚ​ስ​ቱም ጋር መጥቶ እንደ ሆነ ሚስቱ ከእ​ርሱ ጋር ትውጣ።


“ሴት ልጁን ለባ​ር​ነት አሳ​ልፎ የሰጠ ቢኖር ሴቶች ባሪ​ያ​ዎች አር​ነት እን​ደ​ሚ​ወጡ እር​ስዋ ትውጣ።


ፀሐይ ግን ከወ​ጣ​ች​በት የደም ዕዳ አለ​በት፤ የገ​ደ​ለው ይገ​ደል፤ ሌባው ቢያዝ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውም ቢያጣ ስለ ሰረ​ቀው ይሸጥ።


በዚህ ዘመን ሁሉ ግን ባይ​ቤዥ በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት እርሱ ከል​ጆቹ ጋር ይውጣ።


የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ።


በዋጋ ተገ​ዝ​ታ​ች​ኋ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በሥ​ጋ​ችሁ አክ​ብ​ሩት።


“በየ​ሰ​ባቱ ዓመት የዕዳ ምሕ​ረ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ።


እር​ሱ​ንም አር​ነት ባወ​ጣ​ኸው ጊዜ የም​ን​ደ​ኝ​ነ​ቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድ​ርጎ ስድ​ስት ዓመት አገ​ል​ግ​ሎ​ሃ​ልና አያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ት​ሠ​ራው ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።


ሙሴም በዚ​ያች ቀን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት መጨ​ረሻ በም​ሕ​ረት ዓመት በዳስ በዓል፥