ዘዳግም 9:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም በታላቅ ኀይልህ፥ በጸናውና በተዘረጋውም ክንድህ ከግብፅ ምድር ያወጣሃቸው ሕዝብህና ርስትህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እነርሱ በታላቅ ኀይልህና በተዘረጋች ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዝብህና ርስትህ ናቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በታላቅ ኃይልህ በተዘረጋውም ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዝብህና ርስትህ ናቸውና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም ሁሉ በላይ ይህ ሕዝብ ለራስህ ወገን እንዲሆን የመረጥከውና በታላቁ ኀይልህና ብርታትህ ከግብጽ ምድር ያወጣኸው ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም በታላቅ ኃይልህ በተዘረጋውም ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዝብህና ርስትህ ናቸው። |
አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ፥ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ።
አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ዐውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ ይህም ትልቅ ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ዐውቅ ዘንድ ተገለጥልኝ” አለው።
“አቤቱ በፊትህስ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ ሕዝብ አንገተ ደንዳና ነውና ጌታዬ ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ጠማማነታችንን፥ ኀጢአታችንንና በደላችንን ይቅር በለን፤ ለአንተም እንሆናለን” አለ።
ስለዚህም ፈጥነህ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፥ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከግብፃውያንም ተገዥነት አወጣችኋለሁ፤ ከባርነታቸውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ፤ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ፤
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከባቢሎንና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላሜጤን፥ ከምሥራቅና ከምዕራብ ለቀሩት ለሕዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
ምድሪቱን፥ በምድር ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን በታላቅ ኀይሌና በተዘረጋችው ክንዴ ፈጥሬአለሁ፤ ለዐይኔም መልካም ለሆነው እሰጣታለሁ።
አምላካችን እግዚአብሔር በዐይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈተናና በተአምራት፥ በድንቅና በሰልፍ፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ማስፈራራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ገብቶ ለእርሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥
እግዚአብሔርም አለኝ፦ ተነሥተህ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ፤ ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ በድለዋልና፤ ፈጥነው ካዘዝኋቸው መንገድ ፈቀቅ ብለዋልና፥ ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሳቸው አድርገዋልና።
በእግዚአብሔርም ፊት እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፦ የአማልክት ንጉሥ እግዚአብሔር ሆይ፥ በታላቅ ኀይልህ የተቤዠሃቸውን፥ በጠነከረችውም እጅህና በተዘረጋች ክንድህ ከግብፅ ያወጣሃቸውን ሕዝብህንና ርስትህን አታጥፋ።