እርጎና መዓር፥ ያን ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፤ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ያሳልፍላቸው ነበር፤ እነርሱም በሉ።
ዘዳግም 32:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላሙ ቅቤ፥ በበጉም ወተት፥ ከፍየል ጠቦትና ከላም፥ ከጊደሮችና ከበጎች ስብ ጋር፥ ከፍትግ ስንዴ ጋር መገባቸው፤ የዘለላውንም ደም የወይን ጠጅ አድርገው ጠጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወተት፣ የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፣ የባሳንን ምርጥ አውራ በግ፣ መልካም የሆነውንም ስንዴ፣ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ ከሰቡት በጎችና ፍየሎች ጋር፥ የባሳንንም አውራ በጎች፥ ፍየሎችም፥ ከምርጥ ስንዴ ጋር በላህ፥ ከወይኑም ዘለላ የወይን ጠጅ ጠጣህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከከብቶች፥ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ በሚገኝ ወተትና ዕርጎ፥ ከባሳን በሚገኙ ምርጥ ጠቦቶች፥ አውራ በጎች፥ ኰርማዎችና ፍየሎች ጮማ ሥጋ ከምርጥ ስንዴ ዳቦ ጋር መገባቸው። እናንተም ሕዝቦቹ ከቀይ ወይን ዘለላ ጭማቂ የወይን ጠጅ ጠጣችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ 2 ከጠቦት ስብ ጋር፥ 2 የባሳንንም አውራ በግ፥ ፍየሉንም፥ 2 ከስንዴ እሸት ጋር በላህ፤ 2 ከወይኑም ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ። |
እርጎና መዓር፥ ያን ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፤ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ያሳልፍላቸው ነበር፤ እነርሱም በሉ።
አህያይቱን በወይን ግንድ ያስራል፤ የአህያይቱንም ግልገል በወይን ሐረግ፤ ልብሱን በወይን ያጥባል፤ መጐናጸፊያውንም በዘለላው ደም።
ማርና ቅቤ፥ በግና ላም ይበሉ ዘንድ ለዳዊትና ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎች አመጡ። ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርበውና ተጠምተው ደክመው ነበርና።
ምሽጎቹንም ከተሞች፥ መልካምን ነገር የሞሉትን ቤቶች፥ የተማሱትንም ጕድጓዶች፥ የወይኖቹንና የወይራዎቹን ቦታዎች፥ ብዙዎቹንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፤ በሉም፤ ጠገቡም፤ ወፈሩም፤ በታላቅ በጎነትህም ደስ አላቸው።
“ነገር ግን ተመልሰው ዐመፁብህ፤ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፤ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ እጅግም አስቈጡህ።
የኀያላኑን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድርንም አለቆች፥ የአውራ ፍየሎችንና የአውራ በጎችን፥ የወይፈኖችንና፥ የባሳንን ፍሪዳዎች ሁሉ፥ ደም ትጠጣላችሁ።
በሰው ገመድ በፍቅርም እስራት ሳብኋቸው፤ ለእነርሱም ፊቱን በጥፊ እንደሚመቱት ሰው ሆንሁላቸው፤ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እችለውማለሁ።
በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችግረኞችንም የምታስጨንቁ፥ ጌቶቻቸውንም፦ አምጡ እንጠጣ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።
በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
ለእግዚአብሔር ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከስንዴም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤