ዘዳግም 32:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ ከሰቡት በጎችና ፍየሎች ጋር፥ የባሳንንም አውራ በጎች፥ ፍየሎችም፥ ከምርጥ ስንዴ ጋር በላህ፥ ከወይኑም ዘለላ የወይን ጠጅ ጠጣህ።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወተት፣ የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፣ የባሳንን ምርጥ አውራ በግ፣ መልካም የሆነውንም ስንዴ፣ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ከከብቶች፥ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ በሚገኝ ወተትና ዕርጎ፥ ከባሳን በሚገኙ ምርጥ ጠቦቶች፥ አውራ በጎች፥ ኰርማዎችና ፍየሎች ጮማ ሥጋ ከምርጥ ስንዴ ዳቦ ጋር መገባቸው። እናንተም ሕዝቦቹ ከቀይ ወይን ዘለላ ጭማቂ የወይን ጠጅ ጠጣችሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 በላሙ ቅቤ፥ በበጉም ወተት፥ ከፍየል ጠቦትና ከላም፥ ከጊደሮችና ከበጎች ስብ ጋር፥ ከፍትግ ስንዴ ጋር መገባቸው፤ የዘለላውንም ደም የወይን ጠጅ አድርገው ጠጡ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ 2 ከጠቦት ስብ ጋር፥ 2 የባሳንንም አውራ በግ፥ ፍየሉንም፥ 2 ከስንዴ እሸት ጋር በላህ፤ 2 ከወይኑም ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ። Ver Capítulo |