Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 32:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከከብቶች፥ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ በሚገኝ ወተትና ዕርጎ፥ ከባሳን በሚገኙ ምርጥ ጠቦቶች፥ አውራ በጎች፥ ኰርማዎችና ፍየሎች ጮማ ሥጋ ከምርጥ ስንዴ ዳቦ ጋር መገባቸው። እናንተም ሕዝቦቹ ከቀይ ወይን ዘለላ ጭማቂ የወይን ጠጅ ጠጣችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወተት፣ የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፣ የባሳንን ምርጥ አውራ በግ፣ መልካም የሆነውንም ስንዴ፣ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ ከሰቡት በጎችና ፍየሎች ጋር፥ የባሳንንም አውራ በጎች፥ ፍየሎችም፥ ከምርጥ ስንዴ ጋር በላህ፥ ከወይኑም ዘለላ የወይን ጠጅ ጠጣህ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በላሙ ቅቤ፥ በበ​ጉም ወተት፥ ከፍ​የል ጠቦ​ትና ከላም፥ ከጊ​ደ​ሮ​ችና ከበ​ጎች ስብ ጋር፥ ከፍ​ትግ ስንዴ ጋር መገ​ባ​ቸው፤ የዘ​ለ​ላ​ው​ንም ደም የወ​ይን ጠጅ አድ​ር​ገው ጠጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ 2 ከጠቦት ስብ ጋር፥ 2 የባሳንንም አውራ በግ፥ ፍየሉንም፥ 2 ከስንዴ እሸት ጋር በላህ፤ 2 ከወይኑም ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 32:14
22 Referencias Cruzadas  

አብርሃም እርጎ፥ ወተትና ሥጋ ይዞ ሄደና ምግቡን ለእንግዶቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱ ምግቡን በሚበሉበት ጊዜ አብርሃም ከዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ያስተናግዳቸው ነበር።


አህያውን በወይን ግንድ ላይ፥ ውርንጫውን በወይን ሐረግ ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፥ መጐናጸፊያውን እንደ ደም በቀላ የወይን ጭማቂ ያጥባል።


የተመሸጉ ከተሞችንና፥ ለም የሆነችውን ምድር፤ በመልካም ነገር ሁሉ የተሟሉ ቤቶችን፥ የውሃ ጒድጐዶችንና የወይን ተክል ቦታዎችን የወይራና ብዙ የፍሬ ዛፎችን ወረሱ፤ በልተው በመጥገብም ሰውነታቸውን አወፈሩ፤ በቸርነትህ በሰጠሃቸው መልካም ነገር ሁሉ ተደሰቱ።


“ነገር ግን እነርሱ በአንተ ላይ ዐምፀው ለቃልህ አንታዘዝም አሉ፤ ሕግህንም ላለመስማት ፊታቸውን መለሱ፤ በማስጠንቀቅ ወደ አንተ እንዲመለሱ ያስተማሩአቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ በየጊዜውም በአንተ ላይ ክፉ የስድብ ቃል ተናገሩ፤


የወይራ ዘይት እንደ ጐርፍ ሲወርድ፥ ማርና ወተት እንደ ጅረት ውሃ ሲፈስ ሳያይ ይሞታል።


እግሮቼ እንኳ በወተት እስኪታጠቡ ድረስ ብዙ ወተት አገኝ ነበር። የወይራ ዛፎቼም በጭንጫ መሬት ላይ እንኳ ተተክለው እንደ ጐርፍ የሚወርድ ብዙ ዘይት ይሰጡኝ ነበር።


እርሱ ወሰንሽን በሰላም ይጠብቃል፤ በመልካም ስንዴም ያጠግብሻል።


ብዙ ጠላቶች እንደሚዋጉ በሬዎች ከበውኛል፤ እንደ ባሳን ተዋጊ ኰርማዎችም በዙሪያዬ ናቸው፤


እናንተን ግን ጥሩ ስንዴ እመግባችኋለሁ፤ ከአለት ከሚገኘው ማርም አጠግባችኋለሁ።”


እርሱም ክፉውን ነገር ትቶ መልካሙን ነገር ለመምረጥ የሚያስችል ዕውቀት በሚያገኝበት ጊዜ ማርና ወተት ይመገባል።


እነርሱም ከሚሰጡት ብዙ ወተት የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ ያገኛል፤ ከዚህም የተነሣ በምድሪቱ ላይ የሚተርፉ ሰዎች ምግባቸው ማርና ወተት ይሆናል።


እንደ ቅልብ የባሳን ጠቦትና ሙክት ፍየልና ኰርማ የሆኑትን የኀያላን ሰዎችን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድር ልዑላንንም ደም ትጠጣላችሁ።


በሰብአዊ ርኅራኄና በፍቅር ትስስር መራኋቸው፤ ቀንበሩን ከጫንቃቸው ላይ በማንሣት እኔ ራሴ ጐንበስ ብዬ መገብኳቸው።


እንደ ባሳን ቅልብ ላሞች ሰውነታችሁን ያወፈራችሁ የሰማርያ ሴቶች ሆይ! ይህን ቃል አድምጡ! እናንተ ደካሞችን ታዋርዳላችሁ፤ ድኾችን ትጨቊናላችሁ፤ ባሎቻችሁ ሁልጊዜ የሚያሰክር መጠጥ እንዲያቀርቡላችሁ ትጠይቃላችሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! የአንተ መንጋ የሆነውን ሕዝብህን በሥልጣንህ ጠብቅ፤ እነርሱም በለመለመ አትክልት ቦታ መካከል በጫካ ውስጥ ብቻቸውን የሚኖሩ ናቸው፤ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሳንና በገለዓድ እንዲመገቡ አድርጋቸው።


“እስራኤላውያን የሚሰጡኝን ምርጥ የሆነ በኲራት፥ ይኸውም የወይራ ዘይት፥ የወይን ጠጅና እህል ለእናንተ እሰጣችኋለሁ።


እግዚአብሔር በብዙ መንገድ ባርኮህ ነበር፤ አንተ ግን ደስታና ሐሴት በተሞላበት ልብ ሆነህ አላገለገልከውም፤


ከከተማው ውጪ ባለው በወይን መጭመቂያም ተጨመቀ፤ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረስ ልጓም ወደ ላይ ከፍ ያለና ሦስት መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት የሚደርስ ደም ወጥቶ ፈሰሰ።


ሲሣራ “ውሃ አጠጪኝ” አላት፤ እርስዋ ግን ወተት አቀረበችለት፤ በተከበረ ጽዋ እርጎ አመጣችለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos