ባሪያዬም ዳዊት እንዳደረገ፥ ያዘዝሁህን ሁሉ ብትሰማ፥ በመንገዴም ብትሄድ፥ በፊቴም የቀናውን ብታደርግ፥ ትእዛዜንና ሥርዐቴን ብትጠብቅ፥ ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤ ለዳዊትም እንደ ሠራሁለት የታመነ ቤትን እሠራልሃለሁ፤ እስራኤልንም ለአንተ እሰጥሃለሁ።
ዘዳግም 12:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ፥ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ፥ አትብላው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፣ ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላቸው አትብላው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፥ ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላቸው አትብላው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአንተና ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም ይሆንልህ ዘንድ ደምን አትብላ፤ ይህንንም በማድረግህ እግዚአብሔርን ደስ ታሰኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ፥ አትብላው። |
ባሪያዬም ዳዊት እንዳደረገ፥ ያዘዝሁህን ሁሉ ብትሰማ፥ በመንገዴም ብትሄድ፥ በፊቴም የቀናውን ብታደርግ፥ ትእዛዜንና ሥርዐቴን ብትጠብቅ፥ ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤ ለዳዊትም እንደ ሠራሁለት የታመነ ቤትን እሠራልሃለሁ፤ እስራኤልንም ለአንተ እሰጥሃለሁ።
እርሱም፥ “አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም መልካምን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” አለ።
እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበብንና ዕውቀትን፥ ደስታንም ይሰጠዋል፤ ለኀጢአተኛ ግን በእግዚአብሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
የበደለ ከጥንት ጀምሮ ከዚያም በፊት ኀጢአትን አድርጓል፥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት ደኅንነት እንዲሆን አውቃለሁና፤
ክፉ ምክርን መክረዋልና ለነፍሳቸው ወዮላት! እንዲህም አሉ፥ “ጻድቁን እንሻረው፤ ሸክም ሆኖብናልና፤” ስለዚህ የእጃቸውን ሥራ ፍሬ ይበላሉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፤ ዐይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምንም ታፈስሳላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?
በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ፥ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘለዓለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዝህን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምተህ ጠብቅ።
ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቅ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ብታደርግ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ ለእርሱ ልጅ ትሆናለህ።
አንተም በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ባደረግህ ጊዜ የንጹሑን ደም በደል ከመካከላቸው ታርቃለህ።
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ።
በሕይወት እንድትኖሩ፥ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።”
መልካምም ይሆንልህ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርስዋን ትወርስ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን አድርግ።