Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መክብብ 2:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበ​ብ​ንና ዕው​ቀ​ትን፥ ደስ​ታ​ንም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ለኀ​ጢ​አ​ተኛ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እን​ዲ​ሰ​በ​ስ​ብና እን​ዲ​ያ​ከ​ማች ጥረ​ትን ይሰ​ጠ​ዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 አምላክ፣ ደስ ለሚያሠኘው ሰው ጥበብን፣ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። ለኀጢአተኛ ግን፣ አምላክን ደስ ለሚያሠኘው ይተውለት ዘንድ፣ ሀብትን የመሰብሰብና የማከናወን ተግባር ይሰጠዋል። ይህም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እርሱም ደስ ለሚያሰኘው ሰው ጥበብንና እውቀትን ደስታንም ይሰጠዋል፥ ለኃጢአተኛው ግን እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ሥራን ይሰጠዋል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እግዚአብሔር ደስ ለሚያሰኘው ሰው ብቻ ጥበብን፥ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል፤ ለኃጢአተኛ ሰው ግን ድካምን ብቻ ያተርፍለታል፤ ስለዚህም እርሱ ያከማቸውን ሀብት ሁሉ ምንም ላልደከመበት እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኝ ለሌላ ሰው ትቶለት እንዲያልፍ ያደርገዋል፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እርሱም ደስ ለሚያሰኘው ሰው ጥበብንና እውቀትን ደስታንም ይሰጠዋል፥ ለኃጢአተኛ ግን እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 2:26
24 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተ​ሰ​ቦ​ች​ህን ሁሉ ይዘህ ወደ መር​ከብ ግባ፤ በዚህ ትው​ልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይ​ች​ሃ​ለ​ሁና።


ነገር ግን በሟች ሰው ውስጥ መን​ፈስ አለ፥ ሁሉን የሚ​ችል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ስም ያስ​ተ​ም​ራል።


ለሴ​ቶች የፈ​ት​ልን ጥበ​ብና የተ​ለ​ያዩ የጥ​ልፍ ሥራ​ዎ​ችን ዕው​ቀት ማን ሰጠ?


መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ ሥጋ​ህን አን​ጻ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና ስለ ኀጢ​አት የሚ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አል​ወ​ደ​ድ​ሁም።


ጻድ​ቃን አይ​ተው ይፍሩ፤ በእ​ር​ሱም ይሳቁ እን​ዲ​ህም ይበሉ፦


ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥ የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል።


እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከፊቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤


ከሰ​ማ​ይም በታች ስለ​ተ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በጥ​በብ ለመ​መ​ር​መ​ርና ለመ​ፈ​ተን ልቤን አተ​ጋሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይደ​ክ​ሙ​በት ዘንድ ክፉ ድካ​ምን ለሰው ልጆች ሰጥ​ት​ዋ​ልና።


ከፀ​ሐይ በታች የተ​ሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ያለ እርሱ ፈቃድ የሚ​በላ ወይም የሚ​ጠጣ ማን ነው?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ልጆች ይደ​ክ​ሙ​በት ዘንድ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ድካም ሁሉ አይ​ቻ​ለሁ።


ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ።


እስ​ካ​ሁን ምንም በስሜ አል​ለ​መ​ና​ች​ሁም፤ ደስ​ታ​ችሁ ፍጹም ይሆን ዘንድ ለምኑ፤ ታገ​ኙ​ማ​ላ​ችሁ።


ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos