Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 12:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ለአንተና ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም ይሆንልህ ዘንድ ደምን አትብላ፤ ይህንንም በማድረግህ እግዚአብሔርን ደስ ታሰኛለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፣ ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላቸው አትብላው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በጌታ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፥ ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላቸው አትብላው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ነገር ስታ​ደ​ርግ ለአ​ንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ላ​ችሁ፥ አት​ብ​ላው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ፥ አትብላው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 12:25
16 Referencias Cruzadas  

ሁሉ ነገር ስለሚሳካላቸውና የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ጻድቃንን የተባረካችሁ ናችሁ በሉአቸው።


አገልጋዬ ዳዊት እንዳደረገው በፍጹም ልብህ ብትታዘዘኝ፥ በሕጎቼና በትእዛዞቼ ጸንተህ ብትኖር፥ በእኔ ፊት ሞገስ ብታገኝ፥ እኔ ዘወትር ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ በእስራኤል ላይ እንድትነግሥም አደርግሃለሁ፤ ለዳዊት ባደረግሁት ዐይነት ዘሮችህ ከአንተ በኋላ እንደሚነግሡ አረጋግጥልሃለሁ።


እግዚአብሔር አምላካችሁ ለዘለዓለም እንድትኖሩባት በሚያወርሳችሁ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖሩ ዘንድ ለእናንተና ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላቸው እኔ ዛሬ የማዛችሁን ሕጉንና ትእዛዞቹን ጠብቁ።”


እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


ዛሬ እኔ የሰጠሁህን ትእዛዞች ብትጠብቅና እርሱ ከአንተ የሚፈልገውንም ሁሉ ብታደርግ ይህ ተስፋ በእርግጥ ይፈጸምልሃል።


በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክልና መልካም የሆነውን ሁሉ አድርግ፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ ይከናወንልሃል፤ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶችህ በገባውም ተስፋ ቃል መሠረት መልካሚቱን ምድር ትወርሳለህ፤


“እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ሥጋ ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ጣዖት ታመልካላችሁ፤ ግድያ ትፈጽማላችሁ፤ ታዲያ፥ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ እንዴት ምድሪቱ የእኛ ርስት ናት ትላላችሁ?


እግዚአብሔር ደስ ለሚያሰኘው ሰው ብቻ ጥበብን፥ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል፤ ለኃጢአተኛ ሰው ግን ድካምን ብቻ ያተርፍለታል፤ ስለዚህም እርሱ ያከማቸውን ሀብት ሁሉ ምንም ላልደከመበት እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኝ ለሌላ ሰው ትቶለት እንዲያልፍ ያደርገዋል፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።


የደግ ሰው ልጆች በምድር ላይ ብርቱዎች ይሆናሉ፤ የቅኖች ትውልድ ይባረካል።


ለአንተና ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘለዓለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ጠብቅ፤ ይህንንም ስታደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን ነገርን ማድረግህ ነው።


“ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ባዘዝኩህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።


ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ እንዲከናወንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ለረጅም ዘመናት እንድትኖሩ፥ እግዚአብሔር ያዘዛችሁን ሁሉ ፈጽሙ።


ደምን አትብላ፤ ይልቅስ እንደ ውሃ በመሬት ላይ አፍስሰው።


ይኸውም ኃጢአተኞች መቶ ጊዜ ወንጀል ቢሠሩም ለረጅም ዘመን ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔርን ለሚፈሩና ለሚያከብሩ ሁሉ ነገር እንደሚሰምርላቸው ዐውቃለሁ።


በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር ስለምታደርግ ስለ ንጹሑ ሰው ግድያ ወንጀል ተጠያቂ አትሆንም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios