La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 10:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​አ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ህን ታላ​ላ​ቆች የከ​በ​ሩ​ትን ነገ​ሮች ያደ​ረ​ገ​ልህ እርሱ መመ​ኪ​ያ​ችሁ ነው፤ እር​ሱም አም​ላ​ክህ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱ ውዳሴህ ነው፤ በገዛ ዐይኖችህ ያየሃቸውን፣ እነዚያን ታላላቅና አስፈሪ ነገሮች ያደረገልህ አምላክህ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዐይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቅና የሚያስፈሩ ነገሮችን ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱ አምላክህ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱ አምላክህ ነው፤ እርሱ ለአንተ ያደረገልህን ታላላቅና አስደናቂ ነገሮችን ሁሉ በገዛ ዐይኖችህ ስላየህ ዘወትር አመስግነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዓይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቆች የሚያስፈሩትንም ነገሮች ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱም አምላክህ ነው።

Ver Capítulo



ዘዳግም 10:21
18 Referencias Cruzadas  

ለእ​ርሱ ለራሱ እን​ዲ​ሆን ሕዝ​ብን ይቤዥ ዘንድ ለእ​ርሱ ለራ​ሱም ታላቅ ስምን ያደ​ርግ ዘንድ አሕ​ዛ​ብ​ንና ሰፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን በመ​በ​ተን ከግ​ብፅ በተ​ቤ​ዠ​ኸው ሕዝ​ብህ ፊት ታም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መራው እንደ ሕዝ​ብህ እንደ እስ​ራ​ኤል ያለ በም​ድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?


ጌታ ጌታ​ዬን፥ “ጠላ​ቶ​ች​ህን ለእ​ግ​ርህ መረ​ገጫ እስ​ካ​ደ​ር​ግ​ልህ ድረስ በቀኜ ተቀ​መጥ” አለው።


እር​ሱም ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ባሕ​ር​ንም፥ በእ​ነ​ርሱ ውስጥ ያለ​ው​ንም ሁሉ የፈ​ጠረ፤ እው​ነ​ትን ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ጠ​ብቅ፤


የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል፤ የጻ​ድ​ቃ​ኑ​ንም ሁሉ ምስ​ጋና ወደ እርሱ ለቀ​ረበ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።


ነፍ​ሴን መለ​ሳት፥ ስለ ስሙም በጽ​ድቅ መን​ገድ መራኝ።


እኔን ለማ​ዳን ረዳ​ትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አም​ላኬ ነው፤ አመ​ሰ​ግ​ነ​ው​ማ​ለሁ፤ የአ​ባቴ አም​ላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ በሕ​ዝ​ብህ ፊት ሁሉ ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በም​ድር ሁሉ፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያል​ተ​ደ​ረ​ገ​ውን ታላቅ ተአ​ም​ራ​ትን አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፤ እኔም የማ​ደ​ር​ግ​ልህ ነገር ድንቅ ነውና አንተ በመ​ካ​ከሉ ያለ​ህ​በት ይህ ሕዝብ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ያያል።


ፀሐይ በቀን የሚ​ያ​በ​ራ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ በሌ​ሊ​ትም ጨረቃ የሚ​ወ​ጣ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ ለአ​ን​ቺስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም ብር​ሃ​ንሽ፥ አም​ላ​ክ​ሽም ክብ​ርሽ ይሆ​ናል።


የክ​ብ​ር​ህ​ንም ሥራ ባደ​ረ​ግህ ጊዜ፥ ተራ​ሮች በፊ​ትህ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ።


አቤቱ! ፈው​ሰኝ፤ እኔም እፈ​ወ​ሳ​ለሁ፤ አድ​ነኝ፤ እኔም እድ​ና​ለሁ፤ አንተ መመ​ኪ​ያዬ ነህና።


ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃ​ንን፥ ለወ​ገ​ንህ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ክብ​ርን ትገ​ልጥ ዘንድ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሕ​ዛ​ብን ሁሉ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ችን አሳ​ደደ፤ ስለ​ዚህ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን ነውና እኛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን።”


ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።


ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩ፤ ያደ​ረ​ገ​ላ​ች​ሁ​ንም ታላቅ ነገር አይ​ታ​ች​ኋ​ልና በፍ​ጹም ልባ​ችሁ በእ​ው​ነት አም​ል​ኩት፤