መዝሙር 109 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የዳዊት መዝሙር። 1 ጌታ ጌታዬን፥ “ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው። 2 እግዚአብሔር የኀይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል፤ በጠላቶችህም መካከል ትገዛለህ። 3 ቀዳማዊ፦ በኀይል ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን ከአንተ ጋር ነበር፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ። 4 እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ ብሎ፥ እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትምም። 5 እግዚአብሔር በቀኝህ ነው፥ ነገሥታትን በቍጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል። 6 በአሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ ሬሳዎችንም ያበዛል፤ በምድር ላይ የብዙዎችን ራሶች ይቀጠቅጣል። 7 በመንገድ ከፈሳሽ ውኃ ጠጡ፤ ስለዚህ ራስ ከፍ ከፍ ይላል። |