Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 148:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል፤ የጻ​ድ​ቃ​ኑ​ንም ሁሉ ምስ​ጋና ወደ እርሱ ለቀ​ረበ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን አስነሥቷል፤ ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣ እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ፣ ለእስራኤል ልጆች። ሃሌ ሉያ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ የቅዱሳኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል። ሃሌ ሉያ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ለእርሱ ቅርብ የሆኑትን ታማኝ አገልጋዮቹን እስራኤልን ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ ምስጋናንም አቀዳጃቸው። እግዚአብሔርን አመስግኑ!

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 148:14
19 Referencias Cruzadas  

ሰው በፈ​ቃዱ ያመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ልና፥ ከሕ​ሊ​ና​ቸው ትር​ፍም በዓ​ል​ህን ያደ​ር​ጋሉ።


መጥ​ቶም፤ ቀር​በን ለነ​በ​ር​ነው ሰላ​ምን፥ ርቃ​ችሁ ለነ​በ​ራ​ች​ሁት ለእ​ና​ን​ተም ሰላ​ምን ሰጠን።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ን​ጠ​ራው ጊዜ ሁሉ እን​ደ​ሚ​ቀ​ር​በን፥ አም​ላኩ ወደ እርሱ የቀ​ረ​በው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?


ሐናም ጸለ​የች፤ እን​ዲ​ህም አለች፦ “ልቤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸና፤ ቀን​ዴም በአ​ም​ላኬ በመ​ድ​ኀ​ኒቴ ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ተከ​ፈተ፤ በማ​ዳ​ን​ህም ደስ ብሎ​ኛል።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​አ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ህን ታላ​ላ​ቆች የከ​በ​ሩ​ትን ነገ​ሮች ያደ​ረ​ገ​ልህ እርሱ መመ​ኪ​ያ​ችሁ ነው፤ እር​ሱም አም​ላ​ክህ ነው።


መካ​ኒ​ቱን በቤቱ የሚ​ያ​ኖ​ራት፥ ደስ የተ​ሰ​ኘ​ችም የል​ጆች እናት የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት።


አሁን ግን ቀድሞ ርቃ​ችሁ የነ​በ​ራ​ችሁ እና​ንተ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆና​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ደም ቀረ​ባ​ችሁ።


የተ​ጻ​ፈ​ውን ፍርድ በእ​ነ​ርሱ ላይ ያደ​ርግ ዘንድ። ይህች ክብር ለጻ​ድ​ቃኑ ሁሉ ናት።


እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ እና​ንተ ከቅ​ዱ​ሳን ጋር ባላ​ገ​ሮ​ችና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ሰቦች እንጂ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም።


ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃ​ንን፥ ለወ​ገ​ንህ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ክብ​ርን ትገ​ልጥ ዘንድ።”


ኀያ​ላ​ኑን ከዙ​ፋ​ና​ቸው አዋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ትሑ​ታ​ኑ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


አቤቱ! ፈው​ሰኝ፤ እኔም እፈ​ወ​ሳ​ለሁ፤ አድ​ነኝ፤ እኔም እድ​ና​ለሁ፤ አንተ መመ​ኪ​ያዬ ነህና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይነ​ግ​ሣል፤ ጽዮን ሆይ፥ አም​ላ​ክሽ ለልጅ ልጅ ነው።


የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ሃን በላ​ያ​ችን ይሁን። የእ​ጆ​ቻ​ች​ን​ንም ሥራ ያቃ​ና​ል​ናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios