ንጉሥ ሆይ! እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ አንድ ቀን ገላጋይ በሌለበት ስፍራ ሁለቱ ልጆቼ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ አንዱ ሌላውን ገደለው፤
መዝሙር 7:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካላዳንከኝ ግን እንደ አንበሳ ነጥቀው ማንም ሊታደገኝ ወደማይችል ስፍራ ይወስዱኛል፤ ሰባብረውም ያደቁኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤ የሚያድነኝ በሌለበትም ይቦጫጭቁኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴን እንደ አንበሳ እንዳይነጥቋት፥ የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር። |
ንጉሥ ሆይ! እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ አንድ ቀን ገላጋይ በሌለበት ስፍራ ሁለቱ ልጆቼ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ አንዱ ሌላውን ገደለው፤
ስለ ጋድ ነገድም እንዲህ አለ፦ “የጋድን ግዛት ያሰፋ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ ጋድ ክንድን ወይም ግንባርን ለመስበር፥ እንደ አንበሳ ያደባል።
የላይሽ ሕዝብ ከማንም ጋር ግንኙነት ስላልነበራቸውና ከሲዶንም ርቀው ይኖሩ ስለ ነበረ የሚያድናቸው አልተገኘም። ከተማዋ በቤትረሖብ አጠገብ በሚገኝ ሸለቆ ውስጥ ነበረች፤ የዳን ሰዎችም ከተማዋን እንደገና ሠርተው ኖሩባት።