Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 38:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እስከ ንጋት ድረስ ስጮኽ ዐድራለሁ፤ እንደ አንበሳም አጥንቶቼን ሁሉ ሰባበርክ፤ ሌሊትና ቀንም ለሥቃይ አሳልፈህ ሰጠኸኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እስከ ማለዳ በትዕግሥት ጠበቅሁ፤ እርሱ ግን እንደ አንበሳ ዐጥንቶቼን ሁሉ ሰባበረ፤ ከጧት እስከ ማታም ልትጨርሰኝ ፈጠንህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እስኪ ነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፤ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፤ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ፍጻሜዬን አቀረብከው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በዚያ ወራት እስ​ኪ​ነጋ ድረስ እንደ አን​በሳ ታወ​ክሁ፤ እን​ደ​ዚ​ሁም አጥ​ን​ቶች ተቀ​ጠ​ቀ​ጡ​ብኝ፤ ከማ​ለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ተጨ​ነ​ቅሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እስኪነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፥ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 38:13
15 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም ያ ነቢይ “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም እምቢ ስላልክ፥ ከእኔ ተለይተህ እንደ ሄድክ ወዲያውኑ አንድ አንበሳ ይገድልሃል” አለው፤ በእርግጥም ከእርሱ ተለይቶ እንደ ሄደ አንበሳ በድንገት ወደ እርሱ መጥቶ ገደለው።


የዕድሜዬ ቀኖች ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ ይፈጥናሉ፤ ያለ አንዳች ተስፋም ወደ ፍጻሜ ይደርሳሉ።


ቀንና ሌሊት በብርቱ ቀጣኸኝ፤ ርጥበት ያለው ነገር በበጋ ሙቀት እንደሚደርቅ ጒልበቴ በፍጹም አለቀ።


ከጽኑ አመታትህ የተነሣ በጣም ስለ ተዳከምኩ መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ።


“ስለዚህ እናንተ እኔን የምትንቁ ሁሉ ይህን አስተውሉ፤ አለበለዚያ አጠፋችኋለሁ፤ የሚያድናችሁም የለም።


የሰበርካቸውን አጥንቶቼን አድሰህ የደስታንና የሐሤትን ድምፅ አሰማኝ፤


ካላዳንከኝ ግን እንደ አንበሳ ነጥቀው ማንም ሊታደገኝ ወደማይችል ስፍራ ይወስዱኛል፤ ሰባብረውም ያደቁኛል።


ሕይወታችንን ልክ እንደ ሕልም ታሳልፈዋለህ፤ እኛ በየማለዳው እንደሚታደስ የሣር ቡቃያ ነን።


ሥጋዬንና ቆዳዬን አስረጀ፤ አጥንቶቼንም ሰባበረ።


ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።


ከዚህ የተነሣ እስራኤልን እንደ አንበሳ፥ ይሁዳንም እንደ ደቦል አንበሳ በመሆን ሰባብሬአቸው እሄዳለሁ፤ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos