Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ጴጥሮስ 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙሪያችሁ ይንጐራደዳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ራሳችሁን የምትገዙ ሁኑ፣ ንቁም፤ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ዙሪያውን ይንጐራደዳል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በመጠን ኑሩ፤ ንቁም፤ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤

Ver Capítulo Copiar




1 ጴጥሮስ 5:8
61 Referencias Cruzadas  

አስቴርም “ጠላታችንና ሞት የፈረደብንማ ሃማን የተባለው ይህ ክፉ ሰው ነው!” አለችው። ሃማንም እጅግ በመደንገጥ አንዴ ወደ ንጉሡ፥ አንዴ ወደ ንግሥቲቱ ይመለከት ነበር፤


እግዚአብሔርም “ከወዴት መጣህ?” ብሎ ሰይጣንን ጠየቀው። ሰይጣንም “በምድር ዙሪያ ወዲያና ወዲህ እመላለስ ነበር” አለው።


እግዚአብሔር የሚያዘጋጀውን ምግብ ሲያድኑ የአንበሳ ደቦሎች ያገሣሉ።


በእርሱ ላይ የሚፈርድ ዐመፀኛ ዳኛ ሠይም አንዱም ሰው እንዲከስሰው አድርግ፤


የንጉሥ ቊጣ እንደ አንበሳ ጩኸት አስፈሪ ነው፤ ከንጉሥ ዘንድ የሚገኝ ሞገስ ግን ሣርን እንደሚያለመልም ጠል ነው።


የንጉሥ ቊጣ እንደሚያገሣው አንበሳ ያስፈራል፤ የእርሱንም ቊጣ የሚያነሣሣ በራሱ ላይ የሞት ፍርድ እንደ ፈረደ ይቈጠራል።


ድኾችን በጭካኔ የሚገዛ መሪ እንደሚያገሣ አንበሳና ተርቦ ምግቡን ለማደን እንደሚያደባ ድብ ነው።


የሚፈርድልኝ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ ታዲያ ማን ይከሰኛል? የሚከሰኝ ካለ ፊት ለፊት እንገናኝ፤ እስቲ ይቋቋመኝ።


ጠላቶችዋ እንደ ደቦል አንበሳ ያገሡባታል፤ አገርዋን ወደ ምድረ በዳ ለውጠውባታል፤ ከተሞችዋም ተቃጥለው ሰው የማይኖርባቸው ወና ሆነዋል።


ባቢሎናውያን ሁሉ እንደ አንበሳ ያገሣሉ፤ እንደ አንበሳ ደቦልም ያጒረመርማሉ።


ምሽጎቻቸውን ሰባበረ፤ ከተሞቻቸውንም አፈራረሰ፤ እርሱ ባገሣ ቊጥር ምድሪቱና የሚኖሩባት ሰዎች ሁሉ ይሸበራሉ፤


መሪዎቻቸው፥ በገደሉአቸው እንስሶች ዙሪያ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፤ ሕዝቡንም በጭካኔ ይገድላሉ፤ ገንዘብም ሆነ ሌላ ንብረት ያገኙትን ሁሉ ይወስዳሉ፤ በግድያቸውም ብዙዎችን ሴቶች ያለ ባል አስቀርተዋል።


ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።


“እኔ እግዚአብሔር እነርሱን ለማዳን እንደሚያገሣ አንበሳ ድምፄን ሳሰማ እነርሱ ይከተሉኛል፤ ልጆቼም እየተንቀጠቀጡ ከወደ ምዕራብ ይመጣሉ።


ግልገሎችዋ የተወሰዱባት ድብ እንደምታደርግ እኔም አደጋ እጥልባችኋለሁ፤ እቦጫጭቃችሁማለሁ፤ እንደሚባላ አንበሳ እሆንባችኋለሁ፤ እንደሚበጣጥስ ክፉ አውሬም እበጣጥሳችኋለሁ።


እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በኢየሩሳሌም ሆኖ፥ የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤ ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ለእስራኤል መጠጊያ ምሽግ ይሆናል፤


አሞጽ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ሆኖ እንደሚያገሣ አንበሳ የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤ ቃሉም ከኢየሩሳሌም ያስተጋባል፤ እረኞች መንጋ የሚያሰማሩበት መስክ ይጠወልጋል፤ በቀርሜሎስ ተራራ የሚገኘውም ልምላሜ ይደርቃል።”


አንበሳ በደን ውስጥ ዐድኖ የሚበላውን ሳያገኝ በከንቱ ያገሣልን? የአንበሳ ደቦልስ አንዳች ነገር ዐድኖ ሳይዝ በሚኖርበት ቦታ ድምፁን ያሰማልን?


አንበሳ ሲያገሣ ሰምቶ የማይፈራ ማን አለ? ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ሲገልጥለት ትንቢት የማይናገር ማን አለ?


እረኞች ለምለም የሆነ መሰማሪያቸው ስለ ወደመ “ዋይ!” እያሉ ሲያለቅሱ ስሙ፤ የዮርዳኖስን ወንዝ ተከትሎ ያለው የደን መኖሪያቸው ስለ ተደመሰሰ፥ አንበሶች በሐዘን ሲያገሡ ስሙ።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ በራእይ አሳየኝ፤ ሰይጣንም ኢያሱን ለመክሰስ በስተቀኙ ቆሞ ነበር።


እንክርዳዱን የዘራው ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩ የዓለም መጨረሻ ነው፤ ዐጫጆቹ መላእክት ናቸው።


እንግዲህ ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ።


ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!


ከዚህ በኋላ፥ ኢየሱስ በዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ በረሓ ወሰደው።


ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ኢየሱስን ተወው፤ መላእክትም መጥተው አገለገሉት።


ቃሉ በተዘራ ጊዜ በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል የሚወስድባቸውን ሰዎች ነው።


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።


ስለዚህ ከሚመጣው ክፉ ነገር ሁሉ ለማምለጥ ኀይል እንድታገኙና በሰው ልጅ ፊት ለመቆም እንድትችሉ እየጸለያችሁ ዘወትር ትጉ።”


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ስምዖን! ስምዖን! እነሆ፥ ገበሬ ስንዴውን ከገለባ አበጥሮ እንደሚለይ እንዲሁም ሰይጣን እናንተን ሊያበጥራችሁ ፈለገ።


እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል።


ይህንንም የማደርገው የሰይጣንን የተንኰል ሥራ ስለምናውቅ ሰይጣን እንዳያታልለን ብዬ ነው።


ለዲያብሎስም መግቢያ ቀዳዳ አትስጡት።


የዲያብሎስን የተንኰል ሥራ ለመቃወም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን የጦር መሣሪያ በሙሉ ልበሱ።


ነገር ግን ሴት በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ብትጽናና ራስን በመቈጣጠር ብትኖር ልጅ በመውለድ ትድናለች።


እንዲሁም ሴቶች ጠጒርን በማሳመር ወይም በወርቅ ወይም በዕንቊ ወይም ውድ በሆነ ልብስ በማጌጥ ሳይሆን በማፈርና በትሕትና ተገቢ የሆነ የጨዋ ልብስ ይልበሱ።


እንዲሁም ሚስቶቻቸው የተከበሩ፥ ሰውን የማያሙ፥ በመጠን የሚኖሩ፥ በሁሉም ነገር ታማኞች መሆን ይገባቸዋል።


ስለዚህ አንድ ኤጲስ ቆጶስ (የቤተ ክርስቲያን መሪ) ነቀፋ የሌለበት፥ አንዲት ሚስት ብቻ ያገባ፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚገዛ፥ በሥርዓት የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ችሎታ ያለው፥


ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙሉ እንዲነገርና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ ከእኔ ጋር ሆኖ አበረታኝ፤ ከአንበሳም አፍ ድኛለሁ።


ይልቅስ እንግዳ ተቀባይ፥ መልካም የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ ትክክለኛ፥ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ፥ በመጠን የሚኖር ይሁን።


ይህም ጸጋ ክሕደትንና ሥጋዊ ምኞትን በመተው ራስን በመቈጣጠር፥ በቀጥተኛነትና በመንፈሳዊነት በዚህ ዓለም እንድንኖር ያስተምረናል።


በዕድሜ የገፉ ወንዶች፥ በመጠን የሚኖሩ፥ ክብራቸውን የሚጠብቁ፥ ጠንቃቆች፥ በእምነትና በፍቅር በትዕግሥትም ጤናማዎች እንዲሆኑ ምከራቸው።


እንዲሁም ወጣት ሴቶች ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን እንዲወዱ፥


እንዲሁም ጐልማሶች ራሳቸውን በመቈጣጠር እንዲኖሩ ምከራቸው።


ስለዚህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙት፤ እርሱም ከእናንተ ይሸሻል።


ስለዚህ ልቡናችሁን አንቅታችሁ ለሥራ ተዘጋጁ፤ በመጠን ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ለምታገኙት ጸጋ ሙሉ ተስፋ ይኑራችሁ።


እንግዲህ የሁሉ ነገር መጨረሻ ቀርቦአል፤ በትጋት መጸለይ እንድትችሉ የረጋ አእምሮ ይኑራችሁ፤ በመጠንም ኑሩ።


ከዚህ በኋላ አንድ ታላቅ ድምፅ ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “እነሆ አዳኝነት፥ ኀይል፥ መንግሥትም የአምላካችን ሆኖአል! ሥልጣንም የመሲሑ ሆኖአል! ወንድሞቻችንን በአምላካችን ፊት ቀንና ሌሊት ሲያሳጣቸው የነበረ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአል፤


ስለዚህ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ጥቂት ጊዜ ብቻ እንደ ቀረው ስላወቀ ዲያብሎስ በታላቅ ቊጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና ምድርና ባሕር ወዮላችሁ!”


ታላቁም ዘንዶ ወደታች ተጣለ፤ እርሱ መላውን ዓለም የሚያስተው ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው እባብ ነው። እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።


ያሳታቸው ዲያብሎስ፥ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት በዲን በሚቃጠል እሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ፤ በዚያም ሌሊትና ቀን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሠቃያሉ።


ዘንዶውንም ይዞ ሺህ ዓመት አሰረው፤ ይህም ዘንዶ ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን የሚባለው የቀድሞው እባብ ነው፤


ከዚህ በኋላ ሶምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ፤ እዚያም በወይን ተክል ውስጥ አልፈው ሲሄዱ አንድ ደቦል አንበሳ እያገሣ መጣበት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos