ዘኍል 20:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣሉ፦ “በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ለፊት ከቀሩት እስራኤላውያን ወገኖቻችን ጋር ሞተን ቢሆን መልካም በሆነ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴን ተጣሉት፤ እንዲህም አሉት፤ “ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ ምነው እኛም ያኔ ሞተን ባረፍነው ኖሮ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ እንዲህም ብለው ተናገሩት፦ “ወንድሞቻችን በጌታ ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴንም ተጣሉት፤ እንዲህም ብለው ተናገሩት፥ “ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ እንዲህም ብለው ተናገሩት፦ ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ! |
ስለዚህም “የምንጠጣው ውሃ ስጠን” ብለው በሙሴ ላይ አጒረመረሙ። ሙሴም “ስለምን ትወቅሱኛላችሁ? ስለምንስ እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
እስራኤላውያን ስለ ደረሰባቸው ችግር ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ እግዚአብሔርም የማጒረምረም ጩኸታቸውን ሰምቶ እጅግ በመቈጣት የሚባላ እሳት ላከባቸው፤ ያም እሳት ከሰፈሩ አንዱን ክፍል አወደመ።
እግዚአብሔር ወደዚያች ምድር የሚወስደን ለምንድን ነው? እኛ ሁላችን በጦርነት እናልቃለን፤ ሚስቶቻችንና ልጆቻችንም ይማረካሉ፤ ወደ ግብጽ ብንመለስ መልካም አይሆንምን?”