Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሰቈቃወ 4:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የምድር ምርትን በማጣት ቀስ በቀስ በራብ ከመሞት ይልቅ በጦርነት የሚሞቱት የተሻሉ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በራብ ከሚሞቱት ይልቅ፣ በሰይፍ የተገደሉት ይሻላሉ፤ ምግብ በሜዳ ላይ ካለማግኘታቸው የተነሣ፣ በራብ ደርቀው ያልቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጤት። በሰይፍ የሞቱ በራብ ከሞቱት ይሻላሉ፥ እነዚህ የምድርን ፍሬ አጥተው ተወግተውም ቀጥነዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ጤት። በሰ​ይፍ የሞ​ቱት በራብ ከሞ​ቱት ይሻ​ላሉ፤ እነ​ዚህ የም​ድ​ርን ፍሬ አጥ​ተው ተወ​ግ​ተ​ውም ዐል​ፈ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ጤት። በሰይፍ የሞቱ በራብ ከሞቱት ይሻላሉ፥ እነዚህ የምድርን ፍሬ አጥተው ተወግተውም ቀጥነዋል።

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 4:9
10 Referencias Cruzadas  

በዚያው ዓመት አራተኛው ወር በገባ በዘጠነኛው ቀን ራቡ በጣም ስለ ጸና ሕዝቡ የሚመገበው አንዳችም ምግብ አልነበረም።


“ምነው በግብጽ ሳለን እግዚአብሔር በገደለን ኖሮ፥ በዚያ ሌላው ቢቀር ሥጋም ሆነ ሌላ ምግብ የፈለግነውን ያኽል መመገብ እንችል ነበረ፤ እናንተ ግን ሁላችንም በራብ እንድናልቅ ወደዚህ በረሓ አወጣችሁን።”


በሁካታና በጩኸት የተሞላሽ አንቺ ከተማ ሆይ! ሰክረው በመንገዶችሽ ላይ የወደቁት ሰዎች በሰይፍ የተገደሉ ወይም በጦርነት የሞቱ አይደሉም።


ሁሉም በአሠቃቂ በሽታ ያልቃሉ፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ የሚቀብራቸው እንኳ አያገኙም፤ ሬሳቸው እንደ ጒድፍ በሜዳ ላይ ይከመራል፤ በጦርነትና በራብ ያልቃሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ ይሆናል።


ጥምጥማችሁን አታወልቁም፤ ጫማችሁን አውልቃችሁ በባዶ እግራችሁ አትሄዱም፤ አታዝኑም ወይም አታለቅሱም፤ ከኃጢአታችሁም የተነሣ ትመነምናላችሁ፤ እርስ በርሳችሁ በመወያየት ትቃትታላችሁ።


የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፦ “እናንተ በደላችንና ኃጢአታችን ከብደውናል፤ በእነርሱም ምክንያት እየመነመንን ነው፥ ታዲያ እንዴት መኖር እንችላለን ብላችኋል።


ቀጥሎም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ለኢየሩሳሌም የሚቀርበው ምግብ ሁሉ እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝብ በፍርሃትና በስጋት ተሞልተው የሚበሉትን እህልና የሚጠጡትን ውሃ እየመጠኑ እንዲመገቡና እንዲጠጡ አደርጋለሁ።


ውጪ ጦርነት፥ በየቤቱም በሽታና ራብ አለ፤ ከከተማ ውጪ የሚኖር ሁሉ በጦርነት ይሞታል፤ በከተማም ያለ በበሽታና በረሀብ ይመታል።


በጠላቶቻችሁ ምድር ከሞት ተርፋችሁ የምትቀሩት ጥቂቶቻችሁ፥ በራሳችሁና በቀድሞ አባቶቻችሁ ኃጢአት ምክንያት መንምናችሁ ትቀራላችሁ።


እነርሱ ከብትህንና ሰብልህን ሁሉ ጠራርገው ስለሚበሉት እስክትሞት ድረስ በራብ ትቸገራለህ። እነርሱ አንተ እስክትጠፋ ድረስ ከእህልህ አንዲት ፍሬ፥ ከከብትህ ጥጃ፥ ከበጎችህ መንጋ ጠቦት ከወይንህና ከወይራ ዛፍህ ቅንጣት ፍሬ እንኳ አያስተርፉልህም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos