Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 78:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እንዲህ እያሉም በእግዚአብሔር ላይ አጒረመረሙ፤ “እግዚአብሔር በበረሓ ማእድ ዘርግቶ ምግብ ሊሰጥ ይችላልን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እንዲህም ብለው በእግዚአብሔር ላይ ተናገሩ፤ “እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማእድ ማሰናዳት ይችላልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት፦ “እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን?

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 78:19
12 Referencias Cruzadas  

በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።


በሰው እጅ በተሠሩ በሌሎች ሕዝቦች የጣዖት አማልክት ላይ በድፍረት በተናገሩት ዐይነት በኢየሩሳሌም አምላክ ላይም ይናገሩ ነበር።


በመካከላችን ሕገ ወጥ በመሆን፥ በእግዚአብሔር ላይ ንቀትን በማብዛት ኢዮብ በኃጢአቱ ላይ ዐመፅን ጨምሮአል።”


በጠላቶቼ ፊት ታላቅ ማእድ አዘጋጀህልኝ፤ ራሴን በዘይት ትቀባልኛለህ፤ ጽዋዬም እስኪትረፈረፍ ድረስ ይሞላል።


“ምነው በግብጽ ሳለን እግዚአብሔር በገደለን ኖሮ፥ በዚያ ሌላው ቢቀር ሥጋም ሆነ ሌላ ምግብ የፈለግነውን ያኽል መመገብ እንችል ነበረ፤ እናንተ ግን ሁላችንም በራብ እንድናልቅ ወደዚህ በረሓ አወጣችሁን።”


የምንበላውን ሥጋ ስጠን እያሉ ወደ እኔ መጥተው ስለሚያለቅሱ ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ የሚሆን ሥጋ ከወዴት አመጣለሁ?


ከእስራኤላውያን ጋር የሚጓዙ የውጪ አገር ሰዎች ሥጋ ለመብላት የነበራቸው ፍላጎት ከፍተኛ ነበር፤ እስራኤላውያንም እንዲህ እያሉ ማልቀስ ጀመሩ፦ “የምንበላውን ሥጋ ከየት እናገኛለን!


እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣሉ፦ “በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ለፊት ከቀሩት እስራኤላውያን ወገኖቻችን ጋር ሞተን ቢሆን መልካም በሆነ ነበር።


በእግዚአብሔርና በሙሴም ላይ ክፉ ቃል በመናገር እንዲህ ሲሉ አጒረመረሙ፤ “ምግብና ውሃ በሌለበት በዚህ በረሓ እንሞት ዘንድ ከግብጽ ምድር ለምን አወጣችሁን? ይህን አስከፊ ምግብ ሰውነታችን ተጸይፎታል!”


አንተ ሰው! ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ምን መብት አለህ? የሸክላ ዕቃ ሠሪውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ሊለው ይችላልን?


እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔርን ስም፥ መኖሪያውንና በሰማይ የሚኖሩትን መሳደብ ጀመረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos